የነፃነት ድምጽ፤ ዶይቸ ቬለ አማርኛ 50 ዓመት
የዶይቸ ቬለ አማርኛ ቋንቋ ዝግጅት ለመጀመሪያ ጊዜ ዓየር ላይ የዋለው መጋቢት 6 ቀን፣ 1957 ዓ.ም ነበር። በ50 ዓመት የሬዲዮ ስርጭቱ ታሪክ መለስ ብለን ቅኝት እናደርጋለን።
የዶይቸ ቬለ አማርኛ ቋንቋ ስርጭት ወይንም «ራዲዮ ኮሎኝ»
የጣቢያው የቀድሞ ባልደረቦች ሬዲዮ ጣቢያው ቀደም ሲል በሚገኝበት ኮሎኝ ከተማ፥ በታዋቂው የኮሎኝ ካቴድራል ፊት ለፊት፤ ፎቶ 1964 ዓም
የዶይቸ ቬለ የአማርኛ ቋንቋ ባልደረቦች በቀዳሚዎቹ ዓመታት
የአማርኛ ቋንቋ ክፍል ቀዳሚ ባልደረቦች ከያኔው የክፍሉ ኃላፊ ፍራንክ ለምከ ጋር
የጋዜጠኞች ውይይት በ1970ዎቹ ዓመታት
የአማርኛው ክፍል ጋዜጠኞች ውይይት በ1970ዎቹ ዓመታት። ከግራ ወደቀኝ፥ ተክሌ የኋላ፣ ዘውዱ ታደሠ፣ ፍራንክ ለምከ፣ ማቲያስ ዴልትገን፣ አማኑኤል በረከት እና ቦጋለ መኩሪያ
የዶይቸ ቬለ ጋዜጠኞች ጽሑፍ ማርቀቁ ላይ ተመስጠው
መመሰጡ እንደ ኢትዮጵያ ባለ በተጨቆነ የመገናኛ አውታር መድረክ ቀደም ሲልም ሆነ አኹን እጅግ ጠቃሚ ነው።
የዶይቸ ቬለ ጋዜጠኞች ጽሑፍ ማርቀቁ ላይ ተመስጠው
በሚሊዮናት የሚቆጠሩ አድማጮች ተቀያያሪ በሆነው የኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ውስጥ የዶይቸ ቬለ ተከታታይ ሆነው ዘልቀዋል።
ዶይቸ ቬለ የአማርኛ ቋንቋ ስርጭት
ዶይቸ ቬለ የአማርኛ ቋንቋ ስርጭት፤ በአጭር ሞገድ የነፃነት ድምጽ፤ ትናንትም ዛሬም።
ወርቃማ ድምጾች
ጋዜጠኛ ተፈራ ሻውል (በፎቶው በስተቀኝ)ቀዳሚውን «ይኽ ዶይቸ ቬለ ነው» የተሰኘውን የጣቢያውን የሥርጭት መክፈቻ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰማ።
ልዩ እንግዳ በዶይቸ ቬለ ሬዲዮ ጣቢያ
የዶይቸ ቬለ የአፍሪቃው ክፍል የቀድሞ ኃላፊ ማቲያስ ዴልትገን ከእውቁ ኢትዮጵያዊ የእግር ኳስ ጠቢብ (እና የራዲዮ አስተዋዋቂ)ይድነቃቸው ተሰማ ጋር ሲወያዩ
ከሦስት ዓስርት ዓመታት ግድም በኋላ ስንብት
በዶይቸ ቬለ አማርኛ ቋንቋ ክፍል የአድማጮች ማኅደር አዘጋጅ እና አቅራቢ ንጋት ከተማ የመጨረሻውን ቃለ-መጠይቅ ከጋዜጠኛ ኂሩት መለሰ ጋር ስታደርግ
ዶይቸ ቬለ ሬዲዮ አማርኛ በማኅበራዊ መገናኛ ዘርፎችም
ጋዜጠኛ ልደት አበበ እና ማንተጋፍቶት ስለሺ ጣቢያው በአሁኑ ወቅት በሚገኝበት ቦን ከተማ
የአማርኛው ክፍል ባልደረቦች በጋራ
የአማርኛው ክፍል ባልደረቦች ጣቢያው በአሁኑ ወቅት በሚገኝበት የቦን ከተማ፤ ከግራ ወደቀኝ፦ አርያም ተክሌ፣ ንጋት ከተማ፣ ማንተጋፍቶት ስለሺ፣ ሱዛነ በርገርስ፣ መስፍን መኮንን፣ ሸዋዬ ለገሰ፣ አዜብ ታደሰ፣ ኂሩት መለሰ፤ ከበስተኋላ ተክሌ የኋላ፣ ልደት አበበ፣ ሉድገር ሻዶምስኪ፣ ነጋሽ መሐመድ።