1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የነዳጅ ዘይት ዋጋ መጨመር

ሐሙስ፣ ጥቅምት 12 2002

የአንድ በርሜል ነዳጅ ዘይት ዋጋ በትናንቱ ዕለት ወደ ሰማንያ ዶላር ከፍ የማለቱ ዜና ለነዳጅ ዘይት አምራች ለሆኑት ሀገሮች ደስ የሚያሰኝ ሆኖዋል።

https://p.dw.com/p/KCoL
ምስል AP

የዋጋው ጭማሪ እነዚህ ሀገሮችአቋርጠዋቸው የነበሩ አንዳንድ ፕሬዤዎችን እንደገና ሊያነቃቁ የሚችሉበትን ዕድል እንደከፈቱ የነዳጅ ዘይት አምራችና ላኪ ሀገሮች ድርጅት፡ የኦፔክ ዋና ጸሀፊ አብደላ ሳሌም ኧል ባድሪ ገልጸዋል። የዋጋው ጭማሪ ግን ከአንድ ዓመት በፊት ከተከሰተው የፊናንስ ቀውስ በህዋላ የምጣኔ ሀብታቸው እያገገመ ላሉት በኢንዱስትሪ የበለጸጉት እና አዳጊ ሀገሮች ሌላ ችግር እንዳይስከትልባቸው መስጋታቸው አልቀረም።

ነቢዩ ሲራክ/አርያም ተክሌ/ሸዋዬ ለገሰ