1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የነዳጅ ዘይት ዋጋና አፍሪቃ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 9 2001

በወቅቱ በነዳጅ ዘይት ዋጋ ላይ የሚታየው ቅናሽ በዓለም የነዳጅ ዘይት አምራችና ላኪ ሀገሮችን አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ጥሎዋቸዋል። ምክንያቱም የዋጋው ቅነሳ የውጭ ምንዛሪ ገቢያቸውን ዝቅ ማድረጉ አይቀርምና። በአፍሪቃ በሚገኙ የነዳጅ ዘይት አምራች እና ላኪ በሆኑትና መሆን በሚፈልጉት ሀገሮችም ላይ ተጽዕኖ አሳርፎዋል።

https://p.dw.com/p/GJ8b
የነዳጅ ዘይት ቧምቧ በናይጀሪያ
የነዳጅ ዘይት ቧምቧ በናይጀሪያምስል AP

ጋና ውስጥ ባሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ባህር ጠረፍ ላይ ስለተገኘው የነዳጅ ዘይት ንጣፍ ብዙ ሲነገር ይሰማል። ጋና እአአ ከ 2010 ዓም በኋላ የነዳጅ ዘይት ማውጣትና በንግድ ወደ ውጭ መላክዋ እንደማይቀር ይገመታል። ከነዳጅ ዘይት ሽያጭ የሚገኘው ገንዘብም ለሀገሪቱ ጥቅም ሊውል ይችል ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ግምት በርግጥ ተግባራዊ ሊሆን የሚችልበት ትጽቢት መልካም ነው የሚሉት -በብሩናይ ዘጠኝ ዓመት ሙሉ የሰሩት- ጋናዊው የስነ ስበብ ተመራማሪ ክዋበና አናማን እንዳመለከቱት፡ የነዳጅ ዘይት ዋጋ በዓለም ገበያ ላይ የሚወድቅበት ድርጊት በብሄራዊ መንግስታት ፊናንስ በጀት ላይ ከባድ ችግር ያስከትላል።

« የነዳጅ ዘይት ዋጋ በጣም እየቀነሰ ከሄደ፡ የነዳጅ ዘይት የማውጣቱን ስራ ማስፋፋት የማይቻልበትን ስጋት ይደቀናል። ይህም አንዳንድ በዚሁ ስራ ላይ የተሰማሩ የውጭ ኩባንያዎች ለቀው እንዲወጡ ያስገድዳቸዋል። ይህ ዓይነቱ ችግር ቢፈጠር ምን መደረግ እንዳለበት ቀደም ተብሎ ሊታሰብበት ይገባል። እና በነዳጅ ዘይት ምርቱ ላይ የሚወጡ የወደፊት ዕቅዶች ሁሉ የነዳጅ ዘይቱ ዋጋ ሊቀንስ የሚቀንስበት ብሩህ ያልሆነ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ማወቅ ይኖርባቸዋል። »

የነዳጅ ዘይት ዋጋ መቀነስ የጋና ጎረቤት በሆነችው የነዳጅ ዘይት አምራችና ላኪ ሀገር ናይጀሪያ ላይ ከባድ ችግር አስከትሎዋል። ይህችው ሀገር ጠቅኣላላ ያህል ገቢዋን የምታገኘው ከነዳጅ ዘይቱ ሽያጭ ነውና። ባለፈው ህዳር ወር ከነዳጅ ዘይቱ ሽያጭ የተገኘው ገቢ አምና በዚሁ ጊኢዜ ከተገኘው በአንድ ሶስተኛ ዝቅ ብሎ በሀገሪቱ ላይ ወደ አንድ ሚልያርድ ዩሮ ክስረት አድርሶባታል። ችግሩ በተለይ በነዳጅ ዘይቱና በጋዙ ሽያጭ ላይ ጥገኛ የሆነችው ሰሜን አፍሪቃዊቱ ሀገር አልጀሪያ ጎልቶ እንደሚታይ በመዲናይቱ አልዥየ የሚገኘው የጀርመናውያኑ የውጭ ንግድ ድርጅት አንድሬያስሄርገንሮተር አመልክተዋል።

« እርግጥ፡ የነዳጅ ዘይቱ ዋጋ መቀነስ አልጀሪያን በጣም ጎንጦዋል። ይሁኢን እንጂ፡ አልጀሪያ ባለፉት ዓመታት ብዙ የውጭ ምንዛሪ ማከማቸትዋ ሊረሳ አይገባም። በመጨረሻ የወጡ ይፋ መዘርዝሮች እንደሚያሳዩት፡ ይኸው የውጭ ምንዛሪ ክምችት አንድ መቶ ሰላሳ አምስት ዩኤስ ዶላር ነበር። »

በዚሁ የውጭ ምንዛሪ ገቢዋ የሀገርዋን አዳዲስ መንገዶችን እና የባቡር ሀዲዶችን በመገንባት ሀገርዋን ዘመናይ ማድረግ ዓእቅድ አላት። ይሁንና፡ መንግስት ይህንን ዕእእእቅድ ሲወጥን የወጠነው ከነዳጅ ዘይቱ ዋጋ ወደፊትም ከፍ እንዳለ ይቆያል በሚል ግምት ስለነበረ፡ የመሰረተ ልማቱን ለማሻሻል ያደረገውን ዕቅዱን ተግባራዊ ማድረጉን ብዙ ታዛቢዎች ተጠራጥረውታል። የአልጀሪያ የገንዘብ ሚንስትር የነዳጅ ዘይቱ ዋጋ አሁን ከለበት ደረጃ እየቀነሰ ከሄደ ሀገሪቱ መንግስት ያወጣውን የውዒሎተ ንዋይ መርሀ ግብርን እንደገና መማ በስራ ሊተረጎም መቻሉን እንደገና ማጣራት እንደሚኖርባቸው አስታውቀዋል። ባጠቃላይ ሲታይ ግን፡ በነዳጅ ዘይቱ ዋጋ ላይ የተያው ውናሽ አፍሪቃን ያን ያህል እንደማይጎዳ በዓለም ባንክ ውስጥ የአፍሪቃ ኤኮኖሚ ጉዳዮች ተመልካች ክእፍል ኃላፊ ሻንታ ደቫርዣንን የመሳሰሉ የምጣኔ ሀብት ጠበብት ተስፋቸውን ገልጸዋል።

« ሁኔታዎች - የነዳጅ ዘይቱ ዋጋ በጣም ወድቆና በአፍሪቃም ትልቅ ቀውስ አስከትለው ከነበሩት ከሰማንያኛዎቹ ዓመታት የተለዩ እንደሚሆኑ እርጠኞች ነን። ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ የተሻለ ዝግጅት አድርገዋልና። »

በተለይ ጥሬ አላባን በንግድ ወደ ውጭ በመላኩ ተግባር ላይ ጥገኛ የሆኑት ብዙ አፍሪቃውያት ሀገሮች በዓለም ገበያዎች ለሚታየው የዋጋ ጭማሪና ቅናሽ እየተጋለጡ ተገኝተዋል። ይሁን እንጂ፡ ርካሹ የነዳጅ ዘይት የምርትና የኑሮ ወጪን ዝቅ ያደረገበትን ውጤት ማስገኘቱን የምጣኔ ሀብት ጠበብት ገልጸዋል።