የኃይሌ የፕሬዝዳንትነት እቅድና አስተያየት
ረቡዕ፣ ሐምሌ 3 2005ማስታወቂያ
ታዋቂው ኢትዮጵያዊ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር አስቤያለሁ ማለቱ እያነጋገረ ነው። ዴቼቬለ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጭዎች ኃይሌ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ትርጉም ያለው ተፅእኖ የሌለውን የፕሬዝዳንትነት ሥልጣን ከመመኘት ይልቅ ተሰሚነቱን ተጠቅሞ ፋይዳ ያለው አስተዋፅኦ ቢያደርግ ይሻላል ብለዋል። ኃይሌ የሩጫ ችሎታ እንጂ ለፕሬዝዳንትነት የሚያበቃ የፖለቲካ ልምድም ሆነ እውቀቱ እንዳለው እንደሚጠራጠሩ አስተያየት ሰጭዎቹ ተናግረዋል ። ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ