1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቻይና ፕሬዚደንት ለሁለት ሣምንት ጉብኝት ወደ አፍሪቃ አመሩ

ረቡዕ፣ ጥር 23 1999

ቻይናና የኤኮኖሚ ጥቅሟ በአፍሪቃ

https://p.dw.com/p/E0dD
ምስል AP

የቻይና ፕሬዚደንት ሁ ጂንታዎ በአፍሪቃ የሚያካሂዱትን የሁለት ሣምንት ጉብኝት ለመጀመር ወደ ካሜሩን አመሩ። ሁ በአፍሪቃ ቆይታቸው ቻይና ነዳጅ ዘይት የምታወጣባትን ሱዳንን ጨምሮ በጠቅላላው ሥምንት አገሮችን ይጎበኛሉ። ሕዝባዊት ቻይና ባለፉት ዓመታት ከአፍሪቃ አገሮች ጋር ያላትን የኤኮኖሚ ግንኙነት በሰፊው ማጠናከሯ የሚታወቅ ነው። በተፋጠነ የኤኮኖሚ ዕድገት ላይ የምትገኘው ቻይና የኢንዱስትሪ ዘርፏን ጥም ለማብረድ ከአፍሪቃ በተለይ ጥሬ ሃብት ትፈልጋለች። ሁ ጂንታዎ ከ 2003 ዓ.ም. ወዲህ አፍሪቃን ሲገበኙ የአሁኑ ለሶሥተኛ ጊዜ ሲሆን የጉዞው ዓላማ ከክፍለ-ዓለሚቱ ጋር ያለውን የኤኮኖሚና የፖለቲካ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር መሆኑ ተነግሯል። የቻይናው ፕሬዚደንት በሱዳን ቆይታቸው የካርቱም መንግሥት የዳርፉርን ውዝግብ በማብቃቱ ጉዳይ ከተባበሩት መንግሥታት እንዲተባበር ግፊት ያደርጋሉ ተብሎም ይጠበቃል።