1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቻይና ግፊት በሱዳን

ሰኞ፣ የካቲት 17 2000

ቻይና በሱዳን ምዕራባዊ ግዛት ዳርፉር ያለዉ ሰብዓዊ ቀዉስ እልባት እንዲያገኝ በካርቱም መንግስት ላይ የሚገባትን ያህልና አላደረገችም በሚል ትተቻለች።

https://p.dw.com/p/E0ZP
ቻይና በዳርፉር
ቻይና በዳርፉርምስል AP
ይህን የሚያካክስ ተግባር ለመፈፀም በሚልም የልዑካን ቡድኗን ወደሱዳን ልካለች። የልዑካን ቡድኑ የካርቱም መንግስት በተጠቀሰችዉ የአገሪቱ ክፍል ከተመድና ከአፍሪቃ ህብረት የሚዉጣጣዉ ቅይጡ ሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲሰማራ የሚያደርገዉን የማደናቀፍ ተግባር እንዲያቆም ጠይቋል። የዳርፉር አማፅያንም ለዉይይት እንዲቀመጡ ተማፅኗል።