1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቶጎ ውዝግብ እና የአፍሪቃ ኅብረት

ሐሙስ፣ የካቲት 17 1997

ቶጎ በቅርቡ ነፃ ምርጫ የማታደርግ ከሆነ፡ የአውሮጳ ኅብረት ለዚችው ምዕራብ አፍሪቃዊት ሀገር የሚሰጠውን የገንዘብ ርዳታ መቀጠል አለመቀጠሉን እንደሚመረምር ትናንት ከብራስልስ ጽሕፈት ቤቱ የወጣ መግለጫ አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/E0kH
ሟቹ የቶጎ ፕሬዚደንት ግናሲንግቤ ያዴማ
ሟቹ የቶጎ ፕሬዚደንት ግናሲንግቤ ያዴማምስል AP

የማቹ ፕሬዚደንት ልጅ ፎውር ግናስንግቤ አባታቸው ባለው ጥር ሀያ ስምንት ከሞቱ ከሁለት ቀናት በኋላ የሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር ሆነው ቃለ መሀላ የፈፀሙበት ድርጊት ነው ለዚሁ የአውሮጳ ኅብረት ማስጠንቀቂያ ምክንያት የሆነው። በርካታ አፍሪቃውያን መንግሥታት የፎር ግናስንግቤን ሥልጣን መያዝ እንደ መፈንቅለ መነግሥት በመመልከት አውግዘውታል፤ ይሁን እንጂ፡ ራይንሆልት ማየር እንደሚለው፡ ይኸው የማውገዝ ተግባር መንግሥታቱ በሚወሰዱዋቸው ተጨባጭ ርምጃዎች መታየት ይኖርበታል።
በቶጎ የማቹ ፕሬዚደንት ተተኪን በተመለከተ፡ እንዲሁም በኬንያ የፀረ ሙስናው መሥሪያ ቤት ኃላፊ ጆን ጊቶንጎ ሥልጣናቸውን የለቀቁበት ድርጊት በአፍሪቃ አዲስ የልማትና ብልጽግና ዘመን ለመጀመር ተፈንጥቆ ለነበረው ተስፋ ትልቅ እንቅፋት ደቅኖዋል። በዳርፉርና በዚምባብዌ የመረጋጋት ሁኔታ ማስገኘት ያልቻለው የአፍሪቃ ኅብረት፡ በርግጥ ለፀጥታው ፖለቲካ ትልቅ ትኩረት ከሰጠ አሁን በቶጎና ኬንያ ለተፈጠረው ውዝግብ መፍትሔ የማስገኘቱ ጥረቱ መክሸፍ የለበትም። ከከሸፈ በአህጉሩ ልማትና ብልጽግና ለማስገኘት የተሰማውን ተስፋ መና ያስቀረዋል።
በኬንያ በ 1995 ዓም የተደረገው ሰላማዊው የሥልጣን ለውጥ በሀገሪቱ ሥርዓተ ዴሞክራሲን ያነቃቃል፡ ሙሳን ያበቃል እና የኤኮኖሚ ዕድገትን ያስገኛል የሚል ትልቅ ትፅቢት አሳድሮ ነበር። ግን ይህ ለፈላጭ ቆራጭ አምባገነብ መሪዎች ማስጠንቀቂያ ምልክት የሆነው የሥልጣን ለውጥ ወዲያውኑ ነበር መራራውን ጥርጣሬ ያስከተለው። በቶጎም የአውሮጳ ኅብረት የቀድሞው ፕሬዚደንት ግናሲንግቤ ያዴማ በሀገራቸው ምርጫ ለማድረግና ዴሞክራሲያዊውን ሂደት ለመጀመር የገቡትን ቃል ተግባራዊ እንዲያደርጉ ማግባባት የተሳካለት ድርጊት በቶጎ ሕዝብ ዘንድ የብዙ አሠርተ ዓመታት ጭቆናን የሚያበቃበትን ብሩሕ ተስፋ ፈንጥቆ ነበር፤ ይሁንና፡ ይኸው ተስፋ ግናስንግቤ ያዴማ በድንገት ከሞቱና የሀገሪቱ ጦር ኃይልም ሕገ መንግሥቱን በመጣስ ወንድ ልጃቸውን ፎውር ግናስንግቤን ተተኪያቸው ባደረገበት ርምጃው አጥፍቶታል።
በቶጎና በኬንያ ለሚታየው ችግር አፍሪቃውያኑ የሚያስገኙት መፍትሔ ለአህጉሩ ወሳኝ ነው። ለአፍሪቃ ልማት አዲስ አጋርነት፡ ኔፓድ እና የአፍሪቃ ኅብረት አህጉሩን በልማት ራስ አገዝ ለማድረግ፡ ሰብዓዊ መብት እና ሕገ መንግሥትን ለማስከበር፡ እንዲሁም የኤኮኖሚ ዕድገት ለማስገኘት ያስቀመጡዋቸው ዓላማዎች ባዶ ቃላት ሆነው እንዳይቀሩ አፍሪቃውያኑ መንግሥታት ባጣዳፊ ርምጃ መውሰድ ይጠበቅባቸዋል። ካለበለዚያ ምሥቅልቅኩ ሁኔታ፡ ሁከትና ብዙው የአህጉሩ ሕዝብ የሚገኝበትን የድህነት ደረጃ አባብሶ፡ ለአክራሪነትና ለሽብርተኝነት የሚያመቸውን መንሠራሪያ ሁኔታ ይፈጥራል። ለዚህም ነው አፍሪቃውያኑ መንግሥታት ያካባቢ ፀጥታ ጥበቃንና የኤኮኖሚ ትብብርን ለማ?ሻሻል፡ እንዲሁም፡ አፍሪቃውያኑ ድርጅቶች ያካባቢ ውዝግቦች ሳይነሡ በፊት ለማስወገድ ወይም ከተነሡም ሰላማዊ መፍትሔ ለማስገኘት የሚያደርጉትን ጥረት ማጠናከሩ ተገቢ ነው የሚባለው። አፊሪቃውያኑ ፍቱን ውዝግብ ማስወገጃ ደምቦጭ ለማውጣት ዝግጁ ሲሆኑ ብቻ ነው ኔፓድና የአፍሪቃ ኅብረት የተሳካ ውጤት ማስገኘት የሚችሉት። የአፍሪቃ ኅብረት ባወጣው የፀጥታ ፖሊሲ መሠረት፡ አባል ሀገሮች ውዝግብ በሚነሣበት ጊዜ፡ ውዝግቡ ጎረቤት ሀገሮችንም ሊነካ ስለሚችል፡ ባንድነት ኃላፊነት ወስደው መፍትሔ የማፈላለጉን ርምጃ መውሰድ ይኖርባቸዋል። በተለይ፡ በጦር ወንጀል፡ በጎሣ ጭፍጨፋ ወይም በስብዕና አንፃር በሚፈፀሙ ወንጀሎች ወይም ሥርዓተ ዴሞክራሲን ለማናጋት በሚደረጉ ሙከራዎች አንፃር አፍሪቃውያን መንግሥታት ጥጥሩን ርምጃ መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።