1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትናንቱ ብይንና የእንድነት መግለጫ

ሐሙስ፣ ሰኔ 21 2004

በእነ አቶ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በትናንትናው እለት በ24 ተከሳሾች ላይ የተሰጠውን የጥፋተኝነት ብይን እንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ በጥብቅ አወገዘ ። ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ፍርድ ቤቶች ነፃነት የሌላቸው ተቋማት

https://p.dw.com/p/15NiW
***ACHTUNG: Das Foto darf nur für die Rubrik "Der Blick aus meinem Fenster" verwendet werden*** Thema: Der Blick aus meinem Fenster: Addis Abeba, Äthiopien Foto: Solomon Mengist .
ምስል Solomon Mengist

በእነ አቶ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በትናንትናው እለት በ24 ተከሳሾች ላይ የተሰጠውን የጥፋተኝነት ብይን እንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ በጥብቅ አወገዘ ። ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ፍርድ ቤቶች ነፃነት የሌላቸው ተቋማት መሆናቸውን አመልካች ነውም ብሏል ። ፓርቲው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በተለያዩ አጋጣሚዎች በአደባባይ የተናገሩትን የተሳሪዎቹን ጥፋተኝነት ፍርድ ቤቱ በፅሁፍ አንብቦታል ሲልም ፍርዱን ኮንኗል ። በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተገኙት የአቶ አንዷለም አያሌው ባለቤት አቶ አንዷለም ከፍርዱ በኋላ መደብደባቸውን ሲናገሩ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ደግሞ ስንቅ ማቀበል እንደተከለከሉ ለዶቼቬለ ገልፀዋል ። በሌላ በኩል አንድነት በዛሬው መግለጫው የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት የዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑንና ሃገሪቱም ህክምናቸውን መሸፈን አለመቻልዋን አስታውቋል ዝርዝሩን ታደሰ እንግዳው ዝርዝሩን ልኮልናል

ታደሰ እንግዳው

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ