የትሮይ ዴቪስ ሙት-በቃ ብይን ተፈጻሚ መሆን፤11 መስከረም 2004ሐሙስ፣ መስከረም 11 2004ዩናይትድ እስቴትስ ውስጥ ፤ ጆርጂያ ፣ በተባለው ደቡባዊ ፌደራል ክፍለ ሀገር ፣አንድ ፖሊስ ገድለሃል ተብሎ 22 ዓመት በእሥራት ላይ የቆየውና ባልተረጋገጠ ምሥክርነት፣ ሙት-በቃው ብይን የተፈጸመበት ፣ ትሮይ ዴቢስ የተባለው ጥቁር አሜሪካዊ ዜጋ ሁኔታ በዓለም ዙሪያ ቅሬታንም ሆነ ኀዘንን ነው ያስከተለው።https://p.dw.com/p/RnE0ምስል APማስታወቂያ በአውሮፓው ኅብረት ሀገራት ፤ ሙት በቃ ብያኔ የተሰረዘ ሲሆን ፣እንደተጠቀሱት ሃገራት በዴሞክራሲ በምትመራው ሀገር ፣ በዩናይትድ እስቴትስ ግን፤ ሙት-በቃ ህግ ፣ እስካሁን አልተሻረም። በትሮይ ዴቪስ ላይ ተፈጻሚ የሆነውን ሙት- በቃ ብይን አስመልክቶ ፤ ተክሌ የኋላ፤ የዋሽንግተን ዲሲውን ዘጋቢአችንን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግሮታል። አበበ ፈለቀ ተክሌ የኋላ ሒሩት መለሰ