1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትራምፕ የእርዳታ ቅነሳ ዛቻ

ሰኞ፣ መጋቢት 25 2009

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሥልጣን ከያዙ በኋላ መንግሥታቸው ለተለያዩ ሀገራት የሚሰጠውን እርዳታ እንደሚቀንስ ሲዝቱ ነበር ። ትራምፕ ያሉትን ተግባራዊ የሚያደርጉ ከሆነ ከአሜሪካን ከፍተኛ እርዳታ ስታገኝ በቆየችው በኢትዮጵያ ላይ ምን ዓይነት ተጽእኖ ያሳድር ይሆን ?

https://p.dw.com/p/2aZxq
USA Präsident Trump unterzeichnet Dekrete zu Handelsabkommen
ምስል Getty Images/Pool/O. Douliery

Beri AA USAid-Cut für Afrika und die Auswirkungen auf Äthiopien - MP3-Stereo

የረሀብ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ዓምደ መረብ  በያዝነው የጎርጎሮሳውያኑ 2017 ፣ በ45 ሀገራት የሚገኙ 70 ሚሊዮን ያህል ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲል አስታውቋል። ይህን ያህል ህዝብ የአስቸኳይ እርዳታ ጠባቂ በሆነበት በዚህ ወቅት ላይ ብዙ እርዳታ አቅራቢ የሆነችው ዩናይትድ ስቴትስ የምትሰጠው መልስ ማሳሰቡ አልቀረም። የዚህም ምክንያቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሥልጣን ከያዙ በኋላ መንግሥታቸው ለተለያዩ ሀገራት የሚሰጠውን እርዳታ እንደሚቀንስ የሰነዘሩት ዛቻ ነው። ትራምፕ ያሉትን ተግባራዊ የሚያደርጉ ከሆነ ከአሜሪካን ከፍተኛ እርዳታ ስታገኝ በቆየችው በኢትዮጵያ ላይ ምን ዓይነት ተጽእኖ ያሳድር ይሆን ? የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን ስለ ጉዳዩ የኤኮኖሚ ምሁር አነጋግሯል ። 
መክብብ ሸዋ 
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ