የታህሳስ ወር ሃገራዊ እና ባህላዊ ትርጓሜ ክፍል ሁለት
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 16 2007ማስታወቂያ
የታህሳስ ወር ሃገራዊ እና ባህላዊ ትርጓሜ በሚል ርዕስ በተለይ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ በገበሬዉ ዘንድ ስለሚከናወኑ ተግባራትና ስለሚነገሩ ስነ- ቃሎች ባለፈዉ ሳምንት ባቀረብነዉ የመጀመርያ ክፍል ዝግጅት መምህር ካሳይ ገብረ እግዚአብሄርና፤ ሊቀ-ኽሩያን በላይ መኮንን፤ ሰፊ ማብራርያ እንደሰጡን ይታወሳል። በዕለቱ ዝግጅታችን በመፀዉ ወይም መኸር ወቅት በተለይም በኢትዮጵያ ሰብል በሚሰበሰበት በታህሳስ ወር በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የገበሬዉን ህይወት የሚያስቃኙንን ሥነ-ቃሎችና ወጎች እናያለን።