የቲለርሰን ጉብኝት በአዲስ አበባ
ሐሙስ፣ የካቲት 29 2010ማስታወቂያ
የአፍሪቃ ሃገራት ጉብኝታቸዉን በኢትዮጵያ የጀመሩት የዩናይትድ ስቴትስ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን በዛሬዉ እለት አዲስ አበባ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን ሰጡ። ቲለርሰን ቀደም ብለዉ በአፍሪቃ ኅብረት ተገኝተዉ ከኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የአፍሪቃ ሃገራት የገንዘብ ድጋፍ ከሚያደርጉላቸዉ ሃገራት በኩል ያለዉን አካሄድ እንዲያስተዉሉ አሳስበዋል። ቻይና ለአፍሪቃ ሃገራት በችግራቸዉ ወቅት የገንዘብ ድጋፍ ብታደርግም በሥራ ፈጠራዉም ሆነ በስለጠናዉ ረገድ እንደማትራዳ ዋሽንግተን እየተመለከተች መሆኗንም ጠቁመዋል። የአሜሪካዉ ፕሬዝደንት ከወራት በፊት በአፍሪቃ ሃገራት ላይ የሰነዘሩት ጽርፈት ያለፈ ጉዳይ መሆኑን ያመለከቱት ሙሳ ፋኪ በበኩላቸዉ የቲለርሰን ጉብኝት አፍሪቃ እና አሜሪካ ላላቸዉ ግንኙነት ዋና ማሳያ ነዉ ብለዋል። ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ሸዋዬ ለገሠ