1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቴርክ እና ሩሲያ አዲስ ግንኙነት

ሰኞ፣ ነሐሴ 9 2008

ባለፈዉ ኅዳር ወር ቱርክ የሩሲያን የጦር ጀት በሶርያ ድንበሯ አቅራቢያ መትታ ከጣለች በኋላ ለወራት የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ቀዝቅዞ፤ በርቀት ወደ ቃላት ጦርነትም ገብተዉ ቆይተዋል።

https://p.dw.com/p/1JifY
Russland Recep Tayyip Erdogan und Wladimir Putin
ምስል Getty Images/AFP/A. Nemenov

የቴርክ እና ሩሲያ አዲስ ግንኙነት

ሩሲያ ቱርክ ላይ የኤኮኖሚ ማዕቀብ መጣሏ፤ አንካራን ብቻ ሳይሆን ራሷም ላይ ችግር ማስከተሉ አልቀረም። ዉላ አድራ ቱርክ ባለፈዉ ሰኔ ጀቱን ለመጣሏ ይቅርታ ሩሲያን ጠይቃለች። በቅርቡ በፕሬዝደንት ኤርዶኻን መንግሥት ላይ መፈንቅለ ስልጣን ሲሞከር ደግሞ ከሌሎች ሃገራት አስቀድማ ሞስኮ፤ ለቱርክ መንግሥት ሃዘኔታዋን ገለጸች። ይህም ሁለቱ ሃገራት በመካከላቸዉ የተፈጠረዉን መቃቃር አስወግዶ ዳግም ወደ አዲስ ግንኙነት እንዲሻገሩ አድርጓቸዋል። የዕለቱ ማኅደረ ዜና ይህን ይዳስሳል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ