1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቱርካና ሃይቅና ጊቤ ቁጥር 3

ማክሰኞ፣ ሰኔ 8 2002

ጊቤ 3 ለቱርካና ሃይቅ ጥፋት የሚያስከትል በመሆኑ የኬንያ መንግስት በድብቅ ከኢትዮዽያ ሃይል ለመግዛት የሚያደርገው ስምምነት የኬንያ ፍርድ ቤት እንዲያስቆም ተጠየቀ።

https://p.dw.com/p/NrVd
ምስል J. Sorges

የቱርካና ሃይቅ ወዳጆች ማህበር የኬንያን መነግስት ፍርድ ቤት ገትርዋል። ምክንያትቱ ደግሞ የጊቤ ቁጥር 3 ፕሮጀክት የቱርካናን ሃይቅ ሊያጠፋ ይችላል የሚል ነው። የኬንያ መንግስት ከኢትዮዽያ የኤሌክትሪክ ሃይል ለመግዛት የሚል ስሌት ውስጥ ገብቶ ቱርካናንና ማህበረሰቡን ስለዘነጋው ወደፍርድ ቤት መሄዱን የማህበሩ ሊቀመንበር ኢካል አንጌሌ ገልጸዋል። በዚህ ፕሮጀክት የተነሳ ወደ300 ሺህ ኬንያውያን ህይወት አደጋ ውስጥ እንደገባ የገለጸው ማህበሩ ኬንያ ከኢትዮዽያ የደረሰችውን ስምምነት ይፋ እንድታደርግ ፍርድ ቤቱ እንዲያስገድዳት ነው የጠየቀው።

መሳይ መኮንን

ሂሩት መለሰ