የቱርኩ የ AKP ፓርቲ ድልና የኤርዶሀን ዕቅድ
ማክሰኞ፣ ሰኔ 7 2003ማስታወቂያ
ኤርዶጋን በተለያዩ ጊዜያት ባጋጥሙ የፋይናንስ ቀውሶች የሀገሪቱ ምጣኔ ሀብትና ፖለቲካ ተረግግቶ እንዲቀጥል ማስቻላቸው የህዝብ አመኔታን አትርፎላቸዋል ። በርሳቸው አመራር ዘመን ኢኮኖሚው በእጅጉ ተመንድጓል ። በአንድ ወቅት ወደ ፖለቲካው የገባውና በምርጫ ሥልጣን የያዙ መንግሥታትን እንደሻው ያስወግድ የነበረው ወታደሩ ፊቱን ከፖለቲካው እንዲያዞር ማድረጋቸውም ከኤርዶሀን ጉልህ ተግባራት ውስጥ ይደመራል ። እነዚህ ኤርዶሀን ያመጧቸው ለውጦች ለፓርቲያቸው ለ AKP የህዝብ ተወዳጅነትን አትርፈውለታል ።
ሂሩት መለሰ