1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተፈጥሮ አደጋዎችና እስያ

ማክሰኞ፣ መስከረም 26 2002

ሰሞኑን ተከታታይ የተፈጥሮ አደጋዎች በተለያዩ የእስያ ሀገራት እየደረሱ ነዉ።

https://p.dw.com/p/K0G6
ማዕበል ኬትስ በፊሊፒንስምስል AP

ከእነዚህ መካከል ደቡባዊ ህንድን ያጥለቀለቀዉ የጎርፍ አደጋ ላለፉት በርካታ አስርት ዓመታት ያልታየ መሆኑ ነዉ የሚነገረዉ። ጉርፉን ያባባሰዉ ለአምስት ቀናት ያለማቋረጥ የወረደ ከባድ ዝናብ መሆኑ ሲገለፅ ይኸዉ ዝናብ በቀጣይነት አይኖርም ለማለት ግልፅ ማስተማመኛ ምልክት ገና አልተገኘም። በዚህ መዘዝ ግን በርካቶች ከመኖሪያ ቀያቸዉ ተፈናቅለዋል። ኢንዶኔዢያም የመሬት መንቀጥቀጥ በሱማትራ ደሴት ከደረሰባት ከፍተኛ ጉዳት አላገገመችም። ፊሊፒንስና፤ ታይዋንን የነካካዉ ማዕበልም ጃፓንን እንደሚያሰጋ ተነግሯል።

ሸዋዬ ለገሠ፣

ተክሌ የኋላ፣