1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተጠናከረ የጀርመን ነጻ ዴሞክራቶች ፓርቲ፡ ኤፍ ዴ ፔ

ሰኞ፣ መስከረም 18 2002

ትናንት በጀርመን የተካሄደው አጠቃላይ ምክር ቤታዊ ምርጫ ውጤት በትልቆቹ የክርስትያን ዴሞክራቶች ህብረት፡ ሴዴኡ እና በሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲ፡ ኤስ ፔ ዴ መካከል ተቋቁሞ የነበረውን ትልቅ ጥምር መንግስት ፍጻሜ አስከትሎዋል።

https://p.dw.com/p/JqY4
የኤፍ ዴ ፔ ሊቀመንበር ጊዶ ቬስተርቬለ እና መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክልምስል AP

በክርስትያን ዴሞክራቶች ህብረትና በነጻ ዴሞክራቶቹ ፓርቲ መካከል ለሚመሰረት ጥምር መንግስት መንገድ አመቻችቶዋል።

Deutschland Bundestagswahlen 2009 CDU Feier
የመራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ደጋፊዎችምስል picture alliance / dpa

በክርስትያን ዴሞክራቶች ህብረትና በነጻ ዴሞክራቶቹ ፓርቲ መካከል ለሚመሰረት ጥምር መንግስት መንገድ አመቻችቶዋል።

የክርስትያን ዴሞክራቶች ህብረትና የነጻ ዴሞክራቶቹ ፓርቲ በትናንቱ ምርጫ ያስቀመጡትን ዓላማ ከግብ አድርሰዋል። የክርስትያን ዴሞክራቶች ህብረትና እህት ፓርቲው የክርስትያን ሶሻል ህብረት፡ ሴኤስኡ ባንድነት በምርጫው ያገኙት ውጤት (33.8%)ባለፈው ምርጫ ካገኙት አነስ ያለ ቢሆንም፡ በዚሁ ምርጫ ብዙ የመራጭ ድምጽ በማግኘት ከተጠናከረው የነጻ ዴሞክራቶቹ ፓርቲ(14.6%)ር ባንድነት በመሆን ጥምር መንግስት ለመመስረት ይችላሉ። የሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲ ትልቅ ሽንፈት ደርሶባቸዋል።

የሴዲኡ ሊቀመንበርና መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የሁሉም ጀርመናውያን መራሂተ መንግስት የመሆን ዕቅድ እንዳላቸው ከምርጫው ውጤት መታወቅ በኋላ በሰጡት ቃለ ምልልስ አረጋግጠው፡ሁለቱ ወገኖች ዛሬ የመጀመሪያ ውይይት እንደሚያካሂዱ አስታውቀዋል።

ሶሻል ዴሞክራቶቹ ከአራት ዓመት በፊት በተካሄደው አጠቃላይ ምርጫ አግኝተውት ከነበረው የመራጭ ድምጽ በአስራ አንድ ከመቶ ዝቅ ያለ ድምጽ ሲያገኙ(22.9%) ፡ ከሀምሳ ስድስት ዓመት ወዲህ ይህ ዓይነቱ ሽንፈት ሲደርስባቸው ይህ የመጀመሪያው ነው።

በትናንቱ አጠቃላይ ምርጫ ከኤፍዴፔ ሌላ ብዙ የመራጭ ድምጽ በማግኘት የተጠናከሩት ሌሎቹ በምክር ቤት የሚወከሉት የግራ ፓርቲ(12,1%) እና የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ (10,7%) ናቸው።

አርያም ተክሌ