1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተጠርጣሪዎቹ ስሞታና የመንግሥት ማስተባበያ

ረቡዕ፣ ሰኔ 10 2001

የመገናኛ ወይም ኮሚንኬሽን ሚንስትር ደኤታ አቶ ሽመልስ ከማል እንዳሉት ከተጠርጣሪዎቹ ቢያንስ አንዱ ለፍርድ ቤት ያቀረቡት ስሞታ አካላዊ በደል ደርሶብናል የሚል አይደለም።ሚንስትር ደኤታዉ እንደሚሉት ተጠርጣሪዎቹ ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡት የእስር ቤት ይዞታቸዉ ይሻሻል የሚል ነዉ

https://p.dw.com/p/IPu8
ምስል AP GraphicsBank/DW

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናትን ለመግደል፥ የሕዝብ ተቋማትን ለማዉደም አሲረዋል በሚል የታሰሩት ተጠርጣሪዎች መርማሪዎች ፈፅመዉብናል ያሉትን በደል አንድ የመንግሥት ባለሥልጣን አስተባበሉ።የመገናኛ ወይም ኮሚንኬሽን ሚንስትር ደኤታ አቶ ሽመልስ ከማል እንዳሉት ከተጠርጣሪዎቹ ቢያንስ አንዱ ለፍርድ ቤት ያቀረቡት ስሞታ አካላዊ በደል ደርሶብናል የሚል አይደለም።ሚንስትር ደኤታዉ እንደሚሉት ተጠርጣሪዎቹ ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡት የእስር ቤት ይዞታቸዉ ይሻሻል የሚል ነዉ።ታደሰ እንግዳዉ ከአዲስ አበባ ዝር ዝሩን ልኮልናል።

ታደስ እንግዳዉ/ነጋሽ መሐመድ/አርያም ተክሌ