1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተበላሹ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችና አፍሪቃ

ረቡዕ፣ ኅዳር 1 2003

ኮምፕዩተርና የሞባይል ስልኮችን የመሳሰሉ የመረጃ ቴክኖሎጂ ውጤቶች ለአፍሪቃ በርካታ ጥቅሞችን ያስገኛሉ ። ይሁንና የተበላሹ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ወደ አፍሪቃ ሲጣሉ የጤናና የአካባቢ ችግሮችን ማስከተላቸው አይቀርም ።

https://p.dw.com/p/Q5QW
ምስል DW

እነዚህ አገልግሎት መስጠት ያቆሙ ዕቃዎች በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ተሻግረው እንዳይመጡ የሚከላከል ዓለም ዓቀፍ አሰራር ቢኖርም ችግሩን ለማስወገድ ግን በቂ አይደለም ። ይህን መነሻ በማድረግም የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም በክፍለ ዓለሙ ከመቼው ጊዜ በላቀ ሁኔታ እያደገ የመጣውን የተበላሹ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪዎች ክምችት ለማስወገድ የአፍሪቃ አገራት አፋጣኝ ዕርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አስተላልፏል ።

Jane Ayeko

ሂሩት መለሰ