የተቋረጠው የደቡብ ሱዳን የሰላም ንግግር
ዓርብ፣ ነሐሴ 2 2006ማስታወቂያ
የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ከዚህ ቀደም የተቋረጠውን የሰላም ንግግር በዚህ ሳምንት ሰኞ እንደገና ቢቀጥሉም በተከታታይ ቀናት ንግግሩን አላካሄዱም ። ከዚህ ቀደም የተስማሙባቸውን የተኩስ አቁም ውሎችም አሁንም እንደተጣሱ ነው ። በዚህ ሳምንት ሰኞ አዲስ አበባ ውስጥ የተጀመረው የሰላም ንግግር የተቋረጠው ተቃዋሚው SPLM A አንዳንድ ተወካዮች በንግግሩ ላይ መሳተፋቸውን በመቃወሙ መሆኑን የድርድሩ ተካፋይ የሆኑት የሴቶች ተወካይ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። ሁለቱ ወገኖች ንግግሩን እንዲቀጥሉ አደራዳሪው የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን ኢጋድ እየጣረ ነው ።ኢጋድ በተለይ SPLM A በአስቸኳይ ወደ ድርድሩ እንዲመለስ አስጠንቅቋል ። የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አለው ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ