1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተቃውሞ ሰልፍ በጎንደር

ሰኞ፣ ጥር 26 2006

ምንም እንኩዋን የገዢው ፓርቲ ወከባ ቢፈታተነንም ትላንት እሁድ በጎንደር ከተማ የጠራነው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ስኬታማ ነበር ሲል ስማያዊ ፓርቲ ኣስታወቀ። የፓርቲው ም/ሊቀመንበር ዛሬ ለዶቸቬሌ እንደነገሩት መንግስት ከህዝብ እውቅና ውጪ የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን ኣሳልፎ ለመስጠት የያዘውን ስውር ደባ በመቃወም ነበር ስማያዊ ፓርቲ

https://p.dw.com/p/1B28A
Fasil Schloss Gonder Äthiopien
ምስል DW/Azeb Tadesse Hahn

ትላንት ጎንደር ላይ ትዕይንተ ህዝብ የጠራው።

የኢትዮፕያ መንግስት በበኩሉ ይህ ህዝብንn በተሳሳተ መንገድ ለማደናገር የሚካሄድ መሰረተ ቢስ ቅስቀሳ እንጂ ለማንም የተሰጠ ወይንም ሊሰጥ የታሰበ መሬት ፈጽሞ የለም ሲል የፓርቲውን ውንጀላ ኣጣጥሎታል።

የስማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበር እና የምርጫ ጉዳይ ኃላፍ የሆኑት አቶ ስለሺ ፈይሳ እንደሚሉት ኢህኣዲግ መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት የኣገሪቱን ሉዓላዊነት እና የግዛት ኣንድነት በሚጻረር መልኩ የኢትዮጵያን መሬት ኣሳልፎ ለሱዳን እያስረከበ ይገኛል። መጠነ ስፋቱም እንደ አቶ ስለሺ ርዝመቱ 1,600 ኪሜ እና ወርዱ ደግሞ ከ26 እስከ 42 ኪሜ ይደርሳል። ይህንኑ በመቃወም ነበር እንግዲህ አቶ ስለሺ እንደሚሉት ፓርቲያቸው ትላንት በጎንደር ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ የጠራው።

Äthiopien - Premierminister Haile Mariam Desalegne
ምስል CC-BY-SA- World Economic Forum

በህገ መንግስቱ መሰረት ለሰልፉ እውቅና ለማግኘት ለጎንደር ከተማ ማ/ቤት ማመልከቻ ኣቅርበው ተቀባይ ማጣታቸውን የገለጹት አቶ ስለሺ ለቅስቀሳ የተሰማሩ የፓርቲው አባላትም ለተወሰኑ ጊዚያት መታሰራቸውን ኣውስቷል።

ተሰጠ የተባለውን መሬት ኣስመልክቶ ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል ምንም የተገለጸ ነገር የለም የሚሉት የስማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበሩ አቶ ስለሺ ፈይሳ የመረጃ ምንጫቸውንም ለመጠቃቀስ ሞክሯል።

የቀድሞው የጠ/ሚ ጽ/ቤት ቃ/ኣቀባይ እና ኣሁን ደግሞ የጠ/ሚ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ልዩ ረዳት የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ግን ይህ ፈጽሞ ውሸት እና መሰረተ ቢስ ወሬ ነው ሲሉ ኣጣጥለውታል።

በትላንቱ ሰልፍ ላይ የተገኘው ህዝብ ብዛት በእርግጥ፣ ም/ሊቀመንበሩ አቶ ስለሺ ፈይሳ እንደሚሉት፣ የተጠበቀውን ያህል ኣልነበረም። ምክኒያቱ ደግሞ የገዢው ፓርቲ ጫና ሲሆን የሆነ ሆኖ ግን አቶ ኣሉ አቶ ስለሺ ከ ሁለት እስከ ሶስት ሺህ የሚሆኑ ሰልፈኞች ተገኝቷል።

ጃፈር ዓሊ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ