የተቃውሞ ሰልፍ
ረቡዕ፣ መስከረም 25 2009ማስታወቂያ
ጀርመን በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ግፊት እንድታደርግ ተጠየቀች ። በቢሾፍቱ የደረሰውን ሞት በመቃወም ዛሬ የጀርመን ርዕሰ ከተማ በርሊን ሰልፍ የወጡ ኢትዮጵያውያን እና ጀርመናውያን የመብት ተሟጋቾች በቅርቡ ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ ተብለው የሚጠበቁት የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ፣መንግሥት የሰብዓዊ መብት ረገጣን እንዲያቆም ጫና እንዲያደርጉ አሳስበዋል ። አንዳንድ የሰልፉ እንድምተኞች ደግሞ የሜርክል የኢትዮጵያ ጉብኝት ጊዜውን የጠበቀ ስላይደለ ባይሄዱ ይመረጣል ብለዋል ። የሰልፉን ሂደት የተከታተለው የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ዝርዝር ዘገባ አዘግጅቷል .
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ