የተቃውሞ ሰልፍ በበርሊን
ዓርብ፣ ግንቦት 1 2006ማስታወቂያ
በተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተካፈሉት ጀርመን ነዋሪ የሆኑ የኦሮሞ ተወላጆች በወቅቱ ለተፈፀመው የተማሪዎች ግድያ ተጠያቂ ነው ባሉት በኢትዮጵያ በመንግሥት ላይ ጫና እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። የሰልፉ አዘጋጅ ኮሚቴ አባል አቶ ተስፋዬ አብዲሳ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ሰልፈኞቹ ተቃውሞአቸውንጥያቄዎችን የገለጹበትን ደብዳቤ ለጀርመን መንግሥት ለአውሮፓ ህብረትና ለፈረንሳይ መንግሥት ተወካዮች መስጠታቸውን ገልፀዋል። አቶ ተስፋዬን ሂሩት መለሰ አነጋግራቸዋለች።
በተመሳሳይ በዛሬዉ ዕለት የኢትዮጵያዉያን በብራስልስ የአዉሮፓ ኮሚሽን ፊት ለፊት በመገኘት የኢትዮጵያ መንግስት በዜጎቹ ላይ ይፈፅማል ያሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ግድያ፣ እስራትና ማፈናቀል አዉግዘዋል። ሰልፉ የተጠራዉ በዋናነት በአፋር የሰብዓዊ መብት ድርጅት ሲሆን ሉቅማን የኢትዮጵያ እና ቤልጅየም ሙስሊም ማኅበር እና በአዉሮጳ የኢትዮጵያ ግብረኃይል ለፍትህ የተባለ ድርጅትም ተባባሪ የሰልፉ አዘጋጆች መሆናቸዉ ተገልጿል። ተሰላፊዎቹን የቤልጅየም መንግስት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ እንዳነጋገሯቸዉ እና ከአዉሮጳ ኮሚሽን ባለስልጣናት ጋ ለመነጋገርም ቀጠሮ የተያዘ መሆኑን የሰልፉ አስተባባሪ አቶ ጋዐዝ ኑር በብራስልስ ለዶቼ ቬለ ዘጋቢ ገበያዉ ንጉሤ ገልጸዋል።
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ