የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥሪ
ረቡዕ፣ መስከረም 21 2007ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላትና ደጋፊዎች ለታሠሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባላት ያላቸዉን ድጋፍ በግንባር ቀርበዉ እንዲገልጡ የሰወስት ፓርቲ መሪዎች ጠየቁ።የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ፤የሰማያዊና የአረና ትግራይ መሪዎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የታሠሩ አባሎቻቸዉ ነገ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ደጋፊዎችና አባላት በአካል ተገኝተዉ ለእስረኞቹ ያላቸዉን ድጋፍ መግለጥ ይገባቸዋል።መሪዎቹ እክለዉ እንዳስታወቁት እስረኞቹ ፖለቲከኞች ከጠበቃ፤ከቤተሰቦቻቸዉም ሆነ ከፖለቲካ አጋሮቻቸዉ ጋር እንዳይገናኙ ተከልክለዋል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ