የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥሪ
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 22 2005ማስታወቂያ
አቤቱታ ፈራሚ 33 የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ዛሬ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ጥሪ አስተላለፉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሁለንተናዊ ትግል እንዲነሳሳ የ33ቱ አቤቱታ ፈራሚ ፓርቲዎች ጥሪ ያስተላለፉት በአስተባባሪ ኮሚቴያቸው በኩል ነው። ኮሚቴው በውጭ አገራት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ማኅበረሰብም ከጎኑ እንዲቆም ጥሪውን አስተላልፏል። አስተባባሪ ኮሚቴው ይህን የጠየቀው ዛሬ በመኢአድ ጽ/ቤት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነዉ። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር መግለጫውን ተከታትሎታል፤ እንደሚከተለው ያቀርበዋል።
ዮሃንስ ገ/እግዚአብሄር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሃመድ