1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተቃዋሚዉ ፖለቲከኛ ግድያና የኢትዮጵያ መንግሥት አቋም

ረቡዕ፣ የካቲት 24 2002

የፓርቲዉ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ግብሩ አስራት ሟቹ በተደጋጋሚ መታሰራቸዉንና ዛቻም ይፈፀምባቸዉ እንደነበር አስታዉቀዉ ነበር።የኢትዮጵያ ኮምኒኬሽን ሚንስትር አቶ ሽመልስ ከማል ዛሬ እንዳሉት ግን ሰዬዉ የተገደሉት በድንገተኛ ጠብ ነዉ

https://p.dw.com/p/MIie
ምስል AP GraphicsBank/DW

ከትናንት በስቲያ ሌሊት ለዛሬ አጥቢያ ትግራይ መስተዳድር የተገደሉት የተቃዋሚ ፓርቲ አባል አሟሟታቸዉ ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ አይደለም በማለት የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ።በጩቤ ተወግተዉ የሞቱት አቶ አረጋዊ ገብረ ዩሐንስ ተቃዋሚዉን የኢትዮጵያ አንድነትና የዲሞክራሲያዊ መድረክ ወክለዉ ለምክር ቤት አባልነት የሚወዳደሩ እጩ ነበሩ።የፓርቲዉ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ግብሩ አስራት ሟቹ በተደጋጋሚ መታሰራቸዉንና ዛቻም ይፈፀምባቸዉ እንደነበር አስታዉቀዉ ነበር።የኢትዮጵያ ኮምኒኬሽን ሚንስትር አቶ ሽመልስ ከማል ዛሬ እንዳሉት ግን ሰዬዉ የተገደሉት በድንገተኛ ጠብ ነዉ።አቶ ሽመልስን ነጋሽ መሐመድ በስልክ አነጋግሯቸዉ ነበር።አቶ ሽመልስ መንግሥታቸዉ ሥለግድያዉ የሚያዉቀዉን በማስረዳት ይጀምራሉ።

ነጋሽ መሐመድ/ እርያም ተክሌ