የተራዘመዉ የፓሪሱ የአየር ንብረት ተመልካች ጉባዔ
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 1 2008ማስታወቂያ
10 ኛ ቀኑን የያዘዉ ይህ ጉባዔ ሚኒስትሮች በመካከላቸዉ ያለዉን ጥልቅ የሃሳብ ልዩነት ለመፍታት ለሊቱን ሙሉ ቢደራደሩም ነጥብ ላይ ባለመድረሳቸዉ ነዉ ልዩነታቸዉን ለማጥበብ የመጠናቀቅያዉን ቀን ለነገ ቅዳሜ እንዳዛወሩት የተመለከተዉ። ይህን ጉባዔ የሚመሩት የፈረንሳዩ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሎውሮ ፋቢዩስ ዉይይቱ ከተጠበቅነዉ በላይ አንድ አዲስ የመግባብያ ረቂቅ ነጥብ ላይ እንደሚደርስና በቀና መንገድ እየተከናወነ መሆኑን በሙሉ ልብ ተናግረዋል። 195 የዓለም አገራት የሚሳተፉበት የፓሪሱ ጉባዔ የከባቢ አየር ሙቀትን ከ 2,0 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ለመቀነስና ዓለም ላይ ሊከተል የሚቸለዉን አደጋ በመከላከል መፍትሄ ላይ ለመድረስ ነዉ።
ይልማ ኃይለሚካኤል
አዜብ ታደሰ
ሂሩት መለሰ