1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተ.መ. የሰብዓዊ መብቶች ምክርቤት እና ጀርመን

ሰኞ፣ ጥር 25 2001

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ምክርቤት ጄኔቫ ስዊትዘርላንድ ውስጥ ዛሬ በጀመረው ጉባኤ ጀርመንን ጨምሮ የአስራ ስድስት አገራትን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ይገመግማል ።

https://p.dw.com/p/Gls1
ምስል picture-alliance / dpa / AP / Montage DW

ለሁሉት ሳምንታት በሚቆየው በዚሁ ግምገማ ላይ የሚካፈሉት የጀርመን መንግስት ልዑካን የተደባለቀ ስሜት ይዘው ነው ወደ ስብሰባው ያቀኑት ። ጀርመን ዲሞክራሲያዊት አገር እንደመሆንዋ መጠን በህገ መንግስትዋ የሰብዓዊ መብት ጥበቃን በማስፈሯ በግምገማው ሰብዓዊ መብት ጣሽ ናት ተብላ ስለማትወገዝ አያሰጋቸውም ። ሆኖም ታዳጊ ሀገራት ከሚያመዝኑበት ምክርቤት በጀርመን የውጭ መርህ ላይ አትኩረው ለሚነሱ በርካታ አስጨናቂ ጥያቄዎች የጀርመን ልኡካን መዘጋጀት ይኖርባቸዋል ።