1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተመ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዘገባና ኤርትራዉያን ተቃዉሞ

ሰኞ፣ ሰኔ 15 2007

በተለያዩ የአዉሮጳ ሃገራት የሚኖሩ ኤርትራዉያን የዛሬ ሁለት ሳምንት የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ይፋ ያደረገዉን ዘገባ በመቃወም ዛሬ ጄኔቭ ስዊዘርላድ ዉስጥ የተቃዉሞ ሰልፍ አካሄዱ።

https://p.dw.com/p/1FloJ
Schweiz Solidarität mit Eritrea Proteste in Genf
ምስል Sirak Bahlbi


የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኤርትራ መጠነ ሰፊ ቁጥጥርና የጭካኔ ርምጃ ሰበብ ወደ 360 ሺህ የሚጠጉ ዜጎች ወደ አዉሮጳ እንዲሰደዱ መዳረጋቸዉን አስታዉቆ ነበር ። ዛሬ ጄኔቭ ላይ በሺህዎች የሚቆጠሩ ኤርትራዉያን በተቃዉሞ ሰልፉ ላይ እንደተገኙ የገለፁልን አቶ ሲራክ ባህልቢ፤ ክሱ የኤርትራን ሥም ለማጉደፍ የታለመ ፖለቲካዊ ይዘት ያለዉ ባዶ ክስ ነው ሲሉ አስተባብለዋል፤ አቶ ሲራክ በሰልፉ ላይ እንዳሉ በስልክ አነጋግሪያቸው ነበር ። የተቃዉሞ ሰልፉ መልዕክት ምን እንደሆነ በማብራራት ይጀምራሉ ።


አዜብ ታደሰ
ሂሩት መለሰ