1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተመ ወቀሳ በጀርመን የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 29 2005

የተመድ የጠበብት ኮሚቴ የጀርመንን የሰብዓዊ መብት ይዞታ ተቸ። ኮሚቴው በጀርመን ሴቶች በስራው ገበያ ያላቸው አቋም እና ተገን የሚጠይቁ ስደተኞች ሁኔታ አጥጋቢ እንዳልሆነ ከመግለጹ ጎን፡

https://p.dw.com/p/16flX
Vereinte Nationen Logo UN UNO Umweltdossier

በመኖሪያ ቤት ፍለጋ ላይ የውጭ ዜጎች አድልዎ እንደሚደረግባቸው እና በመንከባከቢያ ማዕከላት የሚኖሩ በዕድሜ የጠኑ ሰዎች አዘውትሮ ጥሩ አያያዝ እንደማያገኙ አስታውቋል። ኤሪክ ሴጉንዳ እንደዘገበው፡ 18 አባላት የያዘው ይኸው ኮሚቴ በየአራት ዓመቱ በሚያደርገው ግምገማው ሊደረግ የሚችል መሻሻል ያለውን ጠቁሞዋል።

በጀርመን ሴቶች ከወንዶች አቻዎቻቸው ጋ ቢያንስ እኩል ወይም የበለጠ ችሎታ ቢኖራቸውም በስራው ገበያ ላይ ከፍተኛ ሥልጣን መያዝ ሳይችሉ እንደቀሩ ነው የተመድ ጠበብት ኮሚቴ የገለጸው። ይህንኑ የተመድ ኮሚቴ አባባል የሚጋሩት በጀርመን ፌዴራዊ ምክር ቤት ቡንድስታግ የተወከሉት የአረንጓዴው ፓርቲ እንደራሴ እና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ተመልካች ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበር ወይዘሮ ኢንግሪድ ኸንሊንገር በሀገሪቱ ባሉት 200 ግዙፍ ተቋማት ቦርድ ውስጥ የተወከሉት ሴቶች ቁጥር ሦስት ከመቶ ብቻ መሆኑን ገልጸዋል። ጀርመናውያት ለእኩል ስራ እኩል ደሞዝ አለማግኘታቸውንም ኮሚቴው በመንቀፍ፡ የጀርመን መንግሥት የሴቶችን አቋም ለማሻሻል ተጨማሪ ጥረት እንዲያደርግ ሀሳብ አቅርቦዋል።

ኮሚቴው ከተመለከታቸው ጉዳዮች አንዱ የስደተኞች ጉዳይ ነበር። የጀርመን መሥሪያ ቤቶች ለስደተኞች እና የተገን ማመልከቻ አስገብተው መልስ በመጠበቅ ላይ ላሉት ሁሉ የሕግ ከለላ ሊሰጡ እንደሚገባ ኮሚቴው አሳስቦዋል። እንደ ተመድ ጠበብት ኮሚቴ ውተያየት፡ የተገን ማመልከቻው እየታየ ያለ ስደተኛ እስካሁን እንደሚደረገው ከጀርመን በፊት ወደገባባት  ሀገር በመመለስ ፈንታ፡ በቀጥታ ወደ ጀርመን እንደገቡት ስደተኞች እኩል መብት ሊሰጣቸው ይገባል። በተለይ ፖሊስ የሚፈፅመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳሳሰበው ቢያመለክትም፡ ጥሰቱ የተፈፀመባቸው ያላቸውን ወገኖች በግልጽ አላስታወቀም። በዓመት ምን ያህል ሰው የፖሊስ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ሰላባ መሆኑም አይታወቅም። በዚህም የተነሳ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጀርመን በፖሊስ ይፈፀማል የሚባለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣን ግልጽ እንዲያደርግ ጠይቋል። ይህንኑ ግልጽነት በተመለከተ የጀርመን ፖሊሶች በሚለብሱት መለያ ላይ ቁጥር እንዲፃፍበትና የሰብዓዊ መብት ረገጣ በሚፈፅሙ ፖሊሶች ላይ ክስ ማቅረብ የሚቻልበት ቦታ እንዲከፈት የተመድ ጠበብት ኮሚቴ ሀሳብ አቅርቦዋል። በመንከባከቢያ ማዕከላት የሚኖሩ በዕድሜ የጠኑ ሰዎችም አዘውትሮ ጥሩ አያያዝ እንደማያገኙ፡ ለምሳሌ የማስታወስ ችሎታቸውን ያጡ ወይም ካለርዳታ መንቀሳቀስ የማይችሉትን  ሰዎች ከአልጋቸው ጋ አስሮ ማስቀመጡን ኮሚቴው አክሎ ነቅፎዋል።

Niedersachsen/ ARCHIV: Ein Fluechtling aus Nordafrika traegt in einem Terminal am Flughafen in Hannover - Langenhagen nach seiner Ankunft eine Wollmuetze in den Farben der Deutschen Nationalflagge (Foto vom 11.09.12). Die Zahl der Asylbewerber in Deutschland steigt rasch an. Die staerksten Zuwaechse gibt es dabei bei Migranten aus Serbien und Mazedonien. Das belegen neue Zahlen des Bundesamtes fuer Migration und Fluechtlinge (BAMF), wie die "Bild"-Zeitung (Freitagausgabe vom 12.10.12) berichtet. Demnach wurden allein vom 1. bis 10. Oktober 2012 insgesamt 3.744 Asylantraege gestellt. 1.841 Antraege (49 Prozent) stammten von Serben (1.250) und Mazedoniern (591). Zum Vergleich: Im August stellten Serben und Mazedonier zusammen 1.116 Asylantraege. In der Vergangenheit wurden nach Informationen der Zeitung jedoch weit ueber 90 Prozent dieser Antraege abgelehnt. (zu dapd-Text) Foto: Nigel Treblin/dapd
ምስል dapd

በጀርመን ፀረ አድልዎ ሕግ ያለ አንድ አንቀጽ ቤት አከራይዎች ቤታቸውን የተረጋጋ ማህበራዊ ኑሮን የሚያናጋ ቀውስ እንዳይፈጠር እና የዘር ስብትርን ከግንዛቤ ያስገባ መሆን እንደሚገባው ያዛል። እና የጀርመን ሰብዓዊ መብት ተቋም ባልደረባ ፔትራ ፎልማር ኦቶ እንደምትለው፡ ብዙ አከራዮች ይህን ሰበብ በማድረግ ቤታቸውን ለውሁዳን ቡድን አባላት ላለማከራየት ይጠቀሙበታል። በመሆኑም የተመድ ጠበብት ኮሚቴ ይኸው አንቀጽ እንንዲቀየር ጠይቋል።
የጀርመን መንግሥት ኮሚቴው የሰብዓዊ መብት ይዞታ ማሻሻያ ሲል ስላቀረበው ሀሳብ እስካሁን አስተያየት አልሰጠም። የውጭ ጉዳይም ሆነ የፍትሕ ሚንስቴርም ስለወቀሳው አቋም እንዲወስዱ ከዶይቸ ቬለ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ አልሰጡም። ጀርመን እአአ በ 1976ዓም በስራ ላይ የዋለውን ሲቭል ውል የፈረመች ሀገር እንደመሆንዋ መጠን በውሉ የሰፈሩ ግዴታዎችን እንድታከብር ኢንግሪድ ኸንሊንገር አሳስበዋል። ጀርመን የተመድ ጠበብት ኮሚቴ ያቀረበላትን የማሻሻያ ሀሳቦችን ተግባራዊ ለማድረግ ኮሚቴው ቀጣዩን ዘገባውን እስኪያወጣ ድረስ የአራት ዓመት ጊዜ አላት።

Zwei Beamte der Bundespolizei, von denen einer eine Maschinenpistole in den Haenden haelt (r.), patroullieren am Mittwoch (17.11.10) auf dem Flughafen Leipzig/Halle in der Naehe von Schkeuditz. Bundesinnenminister Thomas de Maiziere (CDU) hat wegen der neuen terroristischen Bedrohungslage in Deutschland eine "sichtbare Polizeipraesenz" angekuendigt. Diese mit den Laendern abgestimmten verschaerften Sicherheitsmassnahmen an Flughaefen und Bahnhoefen sollten "bis auf weiteres" gelten, sagte der CDU-Politiker am Mittwoch in Berlin. (zu dapd-Text) Foto: Jens Schlueter/dapd
ምስል dapd

ኤሪክ ሴጉንዳ/አርያም ተክሌ

ተክሌ የኋላ