1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ

ረቡዕ፣ መስከረም 11 2009

ጉባኤዉ በይፋ ከመጀመሩ ከአንድ ቀን በፊት ባለፈዉ ሰኞ መሪዎቹ፤ ስደተኞችን መርዳት ሥለሚችሉበት ሥልት ተወያይተዋል።ዉይይቱን የመሩት የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ፓን ጊ ሙን ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/1K64N
New York UN Generalversammlung Rede Obama
ምስል picture-alliance/dpa/Li Muzi

[No title]

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 71ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ትናንት ኒዮርክ-ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ በይፋ ተጀምሯል።በጉባኤዉ ላይ የ193ቱ አባል ሐገራት ርዕሰነ ብሔራት፤መራሕያነ መንግሥታት፤ ወይም ተወካዮቻቸዉ ተካፍለዋል።ጉባኤዉ በይፋ ከመጀመሩ ከአንድ ቀን በፊት ባለፈዉ ሰኞ መሪዎቹ፤ ስደተኞችን መርዳት ሥለሚችሉበት ሥልት ተወያይተዋል።ዉይይቱን የመሩት የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ፓን ጊ ሙን ናቸዉ።ያሁኑ ጉባኤ ለኦባማና ለፓን እንደ ፕሬዝደት እና እንደ ዋና ፀሐፊ የመጨረሻቸዉ ነዉ።ፓን በትናንት ንግግራቸዉ ሕገ-መንግሥት እየከለሱ እና ምርጫ እያጭበረበሩ ሥልጣን ላይ «ሙጭጭ» የሚሉ መሪዎችን ወቅሰዋል።

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ