1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተመድ፣ የአፍሪቃ ህብረት እና የሰላም ማስከበሩ ተልዕኮ ምክክር

ረቡዕ፣ ነሐሴ 27 2007

የተመድ እና የአፍሪቃ ህብረት ሰላም የማስከበር ግዴታቸውን መወጣት ስለሚችሉበት ጉዳይ በአዲስ አበባ ምክክር አካሄዱ። ኢትዮጵያ በአህጉሩ ሰላም እና መረጋጋትን ለማስፈን በሚደረጉ ጥረቶች ላይ ወደፊትም ጉልህ ሚና መጫወቷን ትቀጥላለች::

https://p.dw.com/p/1GPjH
Äthiopien Mulatu Teshome ist neuer Präsident
ምስል Elias Asmare/AFP/Getty Images

[No title]

የተመድ እና የአፍሪቃ ሕብረት በአህጉራቱ ሰላም የማስከበር ግዴታቸውን እንዴት መወጣት እንዳለባቸዉ ለማጤን አዲስ አበባ ላይ ተወያዩ። በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰላም እና መረጋጋትን ለማስፈን ስልጣኑ ተሰጦት የተዋቀረዉ የመንግሥታቱ ድርጅት በሰላም አስከባሪዉ ግዳጅ ሲፈተሽ፤ በአህጉራዊ ደረጃ በተለይ በአፍሪቃ አብሮ መሥራትና አዲስ መመርያ አስፈላጊ መሆኑን የሚመክር መድረክ ባለፉት ሁለት ቀናት አዲስ አበባ ላይ ተካሂዷዋል። በስብሰባው ላይ በሰላም አስከባሪ ኃይል ስምሪት ዋነኛ ሚና የያዘችው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት ንግግር አድርገዋል። በቦታዉ ላይ የተገኘው የአዲስ አበባ ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅቶታል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ


አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሃመድ