1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ጉባዔ

ሰኞ፣ መስከረም 9 2009

ዋና መቀመጫዉን ኒዮርክ ያደረገዉ የመንግስታቱ ድርጅት በዚህ በያዝነዉ ሳምንት በስደተኞች ጉዳይ ላይ ያተኮሩ ሁለት ጉባዔዎችን ያካሂዳል። አንደኛው የተመድ ዋና ጸሐፊ ባንኪሙን የጠሩት ጉባኤ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ዩናይትድ ስቴትስ እና ጀርመን በጋራ የጠሩት ጉባኤ ነው ።

https://p.dw.com/p/1K521
USA UN-Gipfel zum Thema Flucht und Migration in New York
ምስል picture alliance/AA/M. Elshamy

[No title]

ጉባዔዎቹ ይህ ነዉ የሚባል መልስ አልያም ነጥብ ላይ ይደርሳሉ ተብሎ ባይጠበቅም 193 የድርጅቱ አባል ሃገራት የስደተኞችና የተገን ጠያቂዎችን አያያዝ በተመለከተ አንድ ፖለቲካዊ ድምዳሜ ላይ ይደርሳሉ የሚል ተስፋ አለ ። ከዚህ ሁሉ ቀደም ሲል ግን የሆሊዉዱ ፊልም የዓለማችን ስደተኞች ቀዉስ አሳሳቢነትን በግልፅ አንፀባርቋል ይላል።
ከጦርነት ከልጆቹ ጋር ፤ እህት፤ ወንድም ፤ ሚስት ባል ፤ መትረፋቸዉን ነዉ የሚናገሩት። ታዋቂዋ የአዉስትራሊያ ፊልም ተዋናይ ኬት ብላንሼት የተወነችበት ፊልም ለተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት አድን ድርጅት «UNICEF» መልስ ለመስጠት ሙከራ የተደረገበት ይመስላል። ይህ ዛሬ ለመጀመርያ ጊዜ በመንግሥታቱ ድርጅት የሚካሄደዉ ጉባዔ ፤ ስደተኞችን በማስፈር ሥራ ላይ ፤ ሕጻናት በእስር አለመያዝ ጉዳይ ላይ፤ እንዲሁም ለስደተኝነት ከሚዳርጉ መሠረታዊ ጉዳዮችን ለመዋጋት የሚረዳ ሃሳብ ላይ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል። በጉባዔዉ የሚሳተፉት 193ቱ አባል ሃገራት በጉባዔዉ ማጠናቀቅያ ፊርማቸዉን ስምምነታቸዉን እንደሚያኖሩም ነዉ የተገለፀዉ።

USA UN-Gipfel zum Thema Flucht und Migration in New York - Ban Ki Moon
ምስል picture alliance/AA/M. Elshamy


« የመንግስታቱ ድርጅት አባል ሃገራት በአንድ ጥሩ ዉጤት ላይ ተስማምተዋል።»
ሲሉ የተመድ ዋና ፀሐፊ ባን ጊ ሙን በስደተኞች ጉዳይ ላይ በአንድ ጉባዔ መጠናቀቅያ ላይ ተናግረዉ ነበር። በለንደን የሚገኘዉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ቢሮ «አምነስቲ ኢንተርናሽናል» ዋና ዳይሪክተር ሪቻርድ ቤንት በበኩላቸዉ ጉዳዩን በሌላ ዓይን ነዉ የሚመለከቱት። ስደተኞችን የማስፈሩ ጉዳይ እየቀነሰ መጥቶአል። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በየዓመቱ ለ10 በመቶ ስደተኞች ቦታ መስጠት የሚል ሃሳብ ያቀረበዉና ይደግፈዉ የነበረዉ የአሰራር ሁኔታ አሁን አይታይም። «አምነስቲ ኢንተርናሽናል» ዋና ዳይሪክተር ሪቻርድ ቤንት እንደሚሉት ስደተኞችን በተመለከተ ተጨባጭ የሆነ ነገር አይታይም ፤ « በአሁኑ ጊዜ የሚታየዉን የስደተኞች ቀዉስ ለመርዳትም ሆነ ለመቅረፍ ፤ ምንም ትክክለኛ የሆነ የተነገረ ነገር የለም፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ምንም ዓይነት ድጋፍም የለም። ጉዳዩን በተመለከተ የሚጠበቀዉን እንዲሁም ያለዉን አመለካከት ተከትሎ እንኳ ቃል የተገባ ነገር እንኳ የለም።»
ስደተኞችን በተመለከተ ዛሬ ኒዮርክ በሚገኘዉ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና መቀመጫ የጀመረዉ ጉባዔ ባለፈዉ አርብ የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት መሪዎች በሕብረቱ የወደፊት ጉዞ ላይ ለመነጋገር ብራቲስላቭ-ስሎቫኪያ ላይ ከተሰበሰቡ በኋላ መሆኑ ነዉ። በዚህ ጉባዔ ስደተኞችን መከፍፈል በሚለዉ ርዕስ ላይ ለፖላንድ፤ ለሃንጋሪ፤ ለቼክና ስሎቫክያ « አመቺ በመሆነ መልኩ ትብብር እንዲያሳዩ» የሚል ሃሳብ ተስተጋብቶአል። ይህ ደግሞ የአዉሮጳ ሃገራት የስደተኞች መከፋፈል መርህ ጋር ምንም ዓይነት ተያያዥነት የለዉም። የሃንጋሪዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቬክቶር ኦርባን ሃገራቸዉ ድንበር ላይ ያቆመችዉ አጥር ለስደተኝነት ቀዉሱ መፍትሄ አድርገዉ ነዉ የሚያዩት። በተመድ ስብሰባ ላይ ከሶርያ የመጡት ስደተኛ ኤሚ ሞሃመድ በዓለም ዙርያ ፎቶግራፉ የተሰራጨዉና በባህር ዳር አሸዋ ላይ በፊቱ ተደፍቶ ሞቶ የተገኘዉን የሦስት ዓመት ሶርያዊ ሕፃን ያስታዉሳሉ፤

USA 71. Gipfel zur Flüchtlinger und Einwanderer der UN
ምስል picture-alliance/AA/M. Elshamy


የተገን ጠያቂዎችና ስደተኞች ጉዳይን በተመለከተ እስከ ጎርጎረሳዉያኑ 2018 ዓ,ም ድረስ አንድ ስምምነት ላይ ይደረሳል ተብሎ ይጠበቃል። አምነስቲ እንተርናሽናል በበኩሉ ይህ ስምምነት በመጭዎቹ ቀናት ቢደረስ ጥሩ ነበር ይላል። ስደተኞችን በተመለከተ ዛሬ ኒዮርክ በሚገኘዉ የተመድ ጉባዔ በኋላ የዩኤስ አሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና፤ የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታየን ማየር፤ በጠሩት ጉባዔ ፤ ሃገራት ስለስደተኞች ክፍፍልና ፤ በፊናንሱ ጉዳይ ላይ ይህ ነዉ የሚባል ነጥብ ላይ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የተመ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፕ ግራዲ ስደተኞችን በተመለከተ በተለይ ድንበራቸዉን በዘጉ ሃገራት ላይ ከፍተኛ ትችትን ሰንዝረዋል።
« በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረገዉ ትብብር አለመሳካቱን እናያለን። ሃገራት ድንበሮቻቸዉን እየዘጉ ናቸዉ። የዉጭ ሃገር ዜጎች ጥላቻ ከምንጊዜዉም በላይ ይስፋፋል። ሰዎች ለደሕንነታቸዉ ሲሉ አደገኛ ጉዞ ዉስጥ ለመግባት ይገደዳሉ። »


ካይ ክሊመንት / አዜብ ታደሰ


ሂሩት መለሰ