1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 3 2009

በሚያቀርባቸዉ ጽሑፎቹና ሃሳቦች ጥፋተኛ ተብሎ የሦስት ዓመት እስር የተፈረደበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደስአለኝ፤ ቤተሰቦቹ የተለያየ ፍርድ ቤት ቢፈልጉትም የለም እየተባሉ መመለስ ከጀመሩ ስድስተኛ ቀን እንደሞላቸዉ ለዶይቼ ቬለ ገለጹ።

https://p.dw.com/p/2U9M2
Temesgen Desalegne
ምስል DW

የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ያነጋገራቸዉና ስማቸዉና ማዕረጋቸዉን መግለፅ እንዳልፈለጉ የተገለጸዉ  አንድ የዝዋይ ማረሚያ ቤት ባልደረባ ግን «የለም የሚባል ነገር የለም፤ ታራሚዉ  እኛ ጋር ነዉ፤ እንደማንኛዉም ታራሚ በክፍሉ ይገኛል።» ሲሉ ተናግረዋል። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ   ከሦስት ዓመት እስር በኋላ ባለፈዉ ጥቅምት 3 ቀን በአመክሮ ይፈታል ተብሎ ቢጠበቅም ከእስር አለመዉጣቱም ተገልጿል።  


ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር 


አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ