የብዝሃ ህይወት ጥበቃና ድህነት5 ግንቦት 2000ማክሰኞ፣ ግንቦት 5 2000ተፈጥሮ ለሰዉ ልጆች የተለያዩ ፀጋዎችን ለግሳለች። ያንን ፀጋ በአግባቡ መጠቀም እየቀረ ያለገደብ ተፈጥሮ ላይ የሚደረገዉ ብዝበዛም እፀዋት እንዲደርቁ፤ ብሎም ዘራቸዉ እንዲጠፋ፤ እንስሳትም በተመሳሳይ መልኩ ለእልቂት እንዲዳረጉ በማስገደዱ፤ ርሃብና ድህነት የሰዉ ልጅን ህይወት ተጎዳኝተዉ መኖር ከጀመሩ ዘመናት ተቆጥረዋል።https://p.dw.com/p/E0mR...............እንዴት ይጠበቅምስል dpaማስታወቂያ በየአቅጣጫዉ ብዝሃ ህይወትን ስለመንከባከብና ስለመጠበቅ ይነገራል፤ በያዝነዉ ዓመት ደግሞ ለየት ባለ መልኩ በሚመስል አካሄድም በተለያዩ ጊዜያት ትላልቅ ጉባኤዎች መካሄድ ይዘዋል። ብዝሃ ህይወትን የመጠበቁ ነገር ታዲያ በተለይ በድሃ አገራት የሚገኘዉን ማህበሰብ ህይወት በማይጎዳ መልኩ እየተደረገ ነዉ ወይ?