የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅትና CPJ
ረቡዕ፣ ግንቦት 8 2004ማስታወቂያ
ዓለም ዓቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት CPJ የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በጋዜጣ አሳታሚዎች ላይ የሚያደርሰውን ጫና ተቃወመ ። CPJ ማተሚያ ቤቱ ለህትመት በሚመጡ ጋዜጦች ላይ የሚወጡ ፅሁፎችን አሳታሚዎች ቅድሚያ ምርመራ እንዲያደርጉባቸው የሚያዝ መመሪያ ማውጣቱ የፕሬስ ነፃነትን የሚፃረር ነው ብሏል ። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የ CPJ የአፍሪቃ ጉዳዮች ባለሞያ የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በጋዜጠኝነት ላይ የቅድሚያ ምርመራ ጫና እያደረገ ነው ሲሉ ተቃውሞአቸውን ተናግረዋል ። አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝሩን ልኮልናል
የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ስላጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጥ የአዲስ አበባው የዶቼቬለ ወኪል ታደሰ እንግዳው ጠይቆ ነበር ። ሆኖም ድርጅቱ መልስ የሚሰጠው በጉዳዩ ላይ ከጋዜጣ አሳታሚዎች ጋር ከተወያየ በኃላ መሆኑን ለወኪላችን አስታውቋል ።
አበበ ፈለቀ
ሒሩት መለሰ
አርያም ተክሌ