1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሪታንያ የምርጫ ዘመቻ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 12 2009

ሜይ መደበኛ ምርጫ በጎርጎሮሳዊው 2020 መካሄድ ቀርቶ ከ7 ሳምንታት በኋላ እንዲካሄድ የፈለጉት ሀገራቸው ከአውሮጳ ህብረት ለመውጣት በምታካሂደው ድርድር ጠንካራ አቋም ይዛ እንድትቀርብ መሆኑን የምርጫ ዘመቻ በተጀመረበት በዛሬው እለት ገልፀዋል።

https://p.dw.com/p/2bcod
Großbritannien Unterhaus Debatte | Theresa May
ምስል picture-alliance/dpa

Beri.London (UK parliament backs early general election) - MP3-Stereo

የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ከወዲሁ ወቅቱን ያልጠበቀ ምርጫ እንዲካሄድ ያቀረቡት ጥያቄ በብሪታንያ ፓርላማ አባላት በከፍተኛ ድምጽ ተቀባይነት ባገኘ በማግስቱ ዛሬ የምርጫ ዘመቻ በይፋ ተጀምሯል።ሜይ መደበኛ ምርጫ በጎርጎሮሳዊው 2020 መካሄድ ቀርቶ ሰኔ 1 2009 ዓም ማለትም ከ7 ሳምንታት በኋላ እንዲካሄድ የፈለጉት ሀገራቸው ከአውሮጳ ህብረት ለመውጣት በምታካሂደው ድርድር ጠንካራ አቋም ይዛ እንድትቀርብ መሆኑን የምርጫ ዘመቻ በተጀመረበት በዛሬው እለት ገልፀዋል።የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነህ ዝርዝሩን ልኮልናል። 
ድልነሳ ጌታነህ 
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ