1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሪታንያ ምርጫ ፣ የመንግስት ምስረታ ውጣ ውረድ እና አስተምህሮቱ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 3 2002

በብሪታኒያ ምርጫ ከተካሄደ 5 ቀናት ቢቆጠሩም እስከዛሬዋ ዕለት ድረስ አዲሱ መንግስት እንዴት እንደሚመሰረትና ማን ሐገሪቱን እንደሚመራ አልታወቀም ።

https://p.dw.com/p/NLX4
ምስል AP Graphics

በሐሙሱ ምርጫ የወግ አጥባቂዎቹ ፓርቲ አብላጫውን የምክር ቤት መቀመጫ አግኝቷል ። ገዥው የሌበር ወይም የሰራተኛ ፓርቲ ደግሞ ሁለተኛውን ደረጃ ሲይዝ ፣ የሊብራል ዲሞክራቶች ወይም የነፃ ዲሞክራቶች ፓርቲ ሶሶተኛውን ስፍራ አግኝቷል ። ምንም እንኳን ወግ አጥባቂው ፓርቲ ከፍተኛውን የምክር ቤት መቀመጫ ቢያገኝም ለገዥነት የሚያበቃውን ቁጥር አለማሟላቱ ለብቻው መንግስት እንዳይመሰረት መሰረታዊ ዕንቅፋት ሆኖበታል ። ታዲያ ከአሁን በኃላ ብሪታኒያ በማን ትመራ ይሆን ? በአሁኑ መንግስት ምስረታ ወሳኙን ድርሻ የያዘው ፣ የነፃ ዲሞክራቶቹ ፓርቲ ከየትኛው ፓርቲ ጋር ለመጣመር ይስማማ ይሆን ? የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን የብሪታንያ ምርጫ ውጤትና የመንግስት ምስረታውን ውጣ ውረድ እንዲሁም አስተምሆሮቱን ይመለከታል ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ