1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሩንዲ መገናኛ ብዙሃንና ጋዜጠኞች ይዞታ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 6 2007

ባለፉት 4 ወራት ውስጥ 80 ጋዜጠኞች ወደ ሩዋንዳና ኬንያ መሰደዳቸው ተዘግቧል ። ጥቃት የተፈፀመባቸውና ዛቻ የተሰነዘረባቸው ጥቂት የሚባሉ አይደሉም ።

https://p.dw.com/p/1GEGw
Symbolbild Burundi Pressefreiheit
ምስል Getty Images/AFP/J. Huxta

[No title]

የብሩንዲው ፕሬዝዳንት ፕየር ንኩሩንዚዛ ባለፈው ግንቦት ለሥስተኛ የሥልጣን ዘመን እንደሚወዳደሩ ሲያሳውቁ ከተነሳው ተቃውሞ ና ግጭት ወዲህ የብሩንዲ መገናኛ ብዙሃንና ጋዜጠኞች ችግር ላይ ወድቀዋል ።በተለይ በንኩሩንዚዛ ላይ ከተካሄደው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በኋላ ብዙ ጋዜጠኞች የታሰሩ ሲሆን በርካቶች ከሃገር ተሰደዋል ።ጥቃት የተፈፀመባቸውና ዛቻ የተሰነዘረባቸውም ጥቂት የሚባሉ አይደሉም ። ባለፉት 4 ወራት ውስጥ 80 ጋዜጠኞች ወደ ሩዋንዳ ታንዛንያና ኬንያ መሰደዳቸው ተዘግቧል ። በአሁኑ ጊዜ የብሩንዲ መገናኛ ብዙሃንና ጋዜጠኞች ይዞታ ምን እንደሚመስል የናይሮቢውን ወኪላችንን ፋሲል ግርማን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ