የብሉናይል ግጭትና የስደተኞች መበራከት
ረቡዕ፣ መስከረም 17 2004ማስታወቂያ
ላለፉት ሶስት ሳምንታት ብቻ ወደሃያ አምስት ሺህ የተገመቱ ሱዳናዉያን ወደኢትዮጵያ መሰደዳቸዉ ሲገለፅ፤ ሌሎች አስር ሺዎችም ሊመጡ እንደሚችሉ ድርጅቱ ከወዲሁ አስታዉቋል። በተጠቀሰዉ አካባቢ የሚታየዉ ግጭት ጦርነት ወደሌሎች አካባቢዎች ሊስፋፋ ይችላል የሚለዉ ስጋትም አይሏል። በኢትዮጵያ የUNHCR ህዝባዊ መረጃ ክፍል ኃላፊን በማነጋገር ሸዋዬ ለገሠ ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅራለች።
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ