የቤይጂንጉ ኦሎምፒክ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 1 2000ማስታወቂያ
አንድ ወር ለቀረው የቤይጂንጉ ኦሎምፒክ ዝግጅቷን ማጠናቀቋን ቻይና አስታወቀች ። በአሁኑ ሰዓት በግንባታ ስራዎች ተሰማርተው የቆዩት የውጭ ዜጎች የመጨረሻ ስራቸውን በማከናወን ላይ ናቸው ። የቻይና ዜና አገልግሎት ሺንዋ እንደዘገበው የዘንድሮው የኦሎምፒክ ጨዋታ ቻይና እንድታስተናግድ መወሰኑ ለቻይና ዓለም ዓቀፍ ስምና ዝና ማንሰራራት ትልቅ አጋጣሚ ሆኗል ። ቻይናው ለአዳዲስ ለመልሶ ግንባታ ያወጣችው ገንዘብ አርባ ቢሊዮን ዶላር ነው ።፡የዝግጅቱ አስተባባሪ ኮሚቴ እንዳስታወቀው ለቤጂንጉ የኦሎምፒክ ጨዋታ ቻይና ሙሉ በሙሉ ዝግጅቷን አጣናቃለች ። እስከ ውድድኡ መክፈቻ ባሉት ቀናት ውስጥም የተራረፉ ስራዎች ይጠናቀቃሉ ።