የቤኔዲግት 16ኛ ጉብኝት የካቶሊክ፦ ሙስሊምና አይሁድ ግንኙነት
ሰኞ፣ ግንቦት 3 2001ማስታወቂያ
የርዕሠ ሊቃነጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ-የሰሞኑ ጉብኝት-መልዕክት ከጳዉሎስ አራተኛ ይልቅ ወደ ዩሐንስ ሃያ-ሰወስተኛ ማዘንበላቸዉን፣ የዳግማዊ ኡርባን፣ የፒዮስ አስረኛን ቃል-ድርጊት ተቃርነዉ የዳግማዊ ጳዉሎስን መርሕ-ምግባር መጋራታቸዉን መስካሪ ነዉ።ሙሴም-ሜርኔፓታሕም፣ክርስቶስ-ጲላጦስም፣ መሐመድ-አቡ ጃሕልም እኩል የኖሩ-ሰናይ-እኩይ የሰበኩ-ያደረጉበት፣ እንደ ራቢን-አረፋት በጎ-ሁሉ፣ የኔታንያሁ-አሕመዲኒጃድ ጥፋት የሚዘራበት ያ! ምድር፣ ቡሽንም-ማንዴላንም-ለተመሳሳይ ስልጣን የሾመዉ የዘመኑ አለም የቤኔዲክት 16ኛን መልዕክት፣የኦባማን ትልም የመቀበል-አለመቀበሉ መሳነት ነዉ ቀቢፀ-ተስፋዉ።ላፍታ-እንዴት ለምን እንላለን አብራችሁኝ ቆዩ።
dw
ነጋሽ መሐመድ/አርያም ተክሌ