1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤኔዲክት አስራ ስድስተኛ የአፍሪቃ ጉብኝት

ማክሰኞ፣ መጋቢት 8 2001

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት አስራ ስድስተኛ በሁለት የአፍሪቃ አገራት የሚያደርጉትን ጉብኝት ለመጀመር ዛሬ ረፋድ ላይ ከቫቲካን ተነስተዋል ።

https://p.dw.com/p/HEGo
ምስል picture-alliance/ dpa

ቤኔዲክት አስራ ስድስተኛ የቤተ ክርስቲያኒቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከሆኑ ወዲህ የመጀመሪያ በሆነው በዚሁ የአፍሪቃ ጉብኛቸው እስከ ፊታችን አርብ ድረስ ካሜሩን የሚቆዩ ሲሆን በመዲናይቱ በያዉንዴም ከአምሳ ሁለት የአፍሪቃ አገራት የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች ጋር ይወያያሉ ። ከዚያም ወደ አንጎላ በማቅናት እዚያ ከሚገኙ ዲፕሎማቶች ጋር ይነጋገራሉ ። ቤኔዲክት አስራ ስድስተኛ በዚሁ ጉብኝታቸው ዓለም ዓቀፉ ማህበሰብ አፍሪቃን እንዳይዘነጋም ጥሪ ያደርጋሉ ። ለዝርዝሩ የሮሙ ዘጋቢያችን ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ