የቤልጂግ ንጉስ ንግግር ያስከተለው ቁጣ
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 19 2005ማስታወቂያ
የቤልጂግ ንጉስ ዳግማዊ አልበርት በገና ዋዜማ ለሃገራቸው ህዝብ ያደረጉት ንግግር ማወዛገቡን ቀጥሏል ። ንጉስ በዚህ ንግግራቸው በአሁኑ ሰአት የተፈጠረውን የኤኮኖሚ ቀውስ መጠቀሚያ በማድረግ ጠባብ የፖለቲካ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ከሚሞክሩ ፖለቲከኞች ህዝቡ እንዲጠነቀቅ ያስተላለፉት መልዕክት NVA የተባለውን የሃገሪቱን ዋነኛ የፖለቲካ ፓርቲ አስቆጥቷል ። የደች ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑትን ፍላንደሮችን ከቤልጂግ ነፃ ማውጣት የሚፈልገው ይኽው ፓርቲ ንጉሱ ገለልተኛ መሆን ሲገባቸው በቀጥታ በፓርቲው ላይ ያነጣጠረ አስተያየት በመስጠታቸው ቁጣውን አስምቷል ። የንጉሱ አስተያየት የፖለቲካ ተንታኞችም ተችተውታል ። ስለአወዛጋቢው የንጉስ አልበርት ንግግር የብራሰልሱን ዘጋቢያችንን ገበያው ንጉሴን ስቱድዮ ከመግባታችን በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
ገበያው ንጉሴ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ