የባህር ወንበዴዎችና ሂዝቡል ኢስላም
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 27 2002ማስታወቂያ
ይህ አክራሪ ቡድን ሃርዴርን በእጁ እንዳስገባ የሸሪዓ ህግ ተግባራዊ እንዲሆን አውጇል። ያለምንም የተኩስ ልውውጥ ሃርዴርን የተቆጣጠረው ሂዝቡል፤ ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው ይታመናል። መሪው ሼክ ዳሂር አዌስ ከእስላማዊው የፍርድ ቤቶች ህብረት መበተን በኋላ ሂዝቡልን ይዘው ዳግም ሶማልያን ለመቆጣጠር እየገሰገሱ ነው። ባለፈው ሰኞ ሃርዴርን ከወንበዴዎች ካስለቀቁ በኋላ የበላይነትን እያገኙ ነው። አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው የባህር ላይ ወንበዴዎቹ ለጊዜው ከሃርዴር ሸሽተዋል። በሂዝቡል ድል የሃርዴርም ሆኑ የሞቃዲሾ ነዋሪዎች ደስተኞች እንደሆኑ ተዘግብዋል።
መሳይ መኮንን
ሸዋዩ ለገሠ