1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የባህል ጥንቅር

ሰኞ፣ ግንቦት 23 2002

የለቱ የባህል ቅንብራችን ባሳለፍነዉ ሳምንት በፈረንሳይ ካን ስለተካሄደዉ የፊልም ፊስቲቫል እንዲሁም በጀርመን በሳምንቱ ዉስጥ ስለነበሩ ባህል ጠቀስ ክንዉኖች በክፍል አንድ ጥንቅሩ ያካተተ ሲሆን በክፍል ሁለት ጥንቅሩ በኢትዮጽያችን በተለይ የናይሎ ሰሃራ ቋንቋ ዝርያን ተናጋሪ ናቸዉ

https://p.dw.com/p/NdHz
ምስል Afro Project

ተብለዉ ከሚጠቀሱት ሃያ ሁለት ብሄረሰቦች መካከል የኖር ብሄረሰቦችን ባህላዊ የግጭት መፍቻ እና ሰላም መጠበቅያ ዘዴ እናያለን ለጥንቅሩ አዜብ ታደሰ ነኝ መልካም ቆይታ!

የጀርመን አዋሳኝ በሆነችዉ በፈረንሳይ ለሁለት ሳምንት ያህል የዘለቀዉ የካን አለም አቀፍ የፊልም ፊስቲቫል ባለፈዉ እሁድ ተጠቃልሏል። ዘንድሮ 63 ኛ ግዜ የተካሄደዉ ይህ ፊልም ፊስቲቫል በአሸናፊነት የታይላንዱን ፊልም ማግኘቱ ሁኔታዉን አስገራሚ አድርጎታል።
አጎቴ ቡኔ የሚል ስያሜን የያዘዉ ይህ አሸናፊ ፊልም በዳግም ህይወት የሚያምኑ አንድ በጠና የታመሙ አዛዉንት በሞት የተለየቻቸዉን ባለቤታቸዉን እና በጦርነት ሰበብ የጠፋባቸዉን ልጃቸዉን ዳግም ሲያገኙ እንዲሁም አዛዉንቱ የወጣትነት ህይወታቸዉን ሲያስቡ ይተርካል። ፊልሙ በተለይ የፖለቲካ ብጥብጥ ባለበት በታይላንድ የፊል ትረካዉ እንደ አንድ ሰላም ማድረሻ መልክተኛ እንዲሆን የታሰበ ነዉም ተብሎለታል። የሰላሳ ዘጠኝ አመቱ ታይላንዳዊዉ የፊልም ስራ አዋቂ አጎቴ ቡኔ ለተሰኘዉ ፊልሙ በአዉሮጻ ቁጥር አንድ የተባለዉን የዘንባባ ዝንጣፊ መሰል ቅርጽ ያለዉን የወርቅ ሽልማት ሲወስድ በኮለኝ የሚገኘዉ ማች ፍክትሪ የተሰኘዉ ጀርመናዉያን የፊልም ስራ ኩባንያም በታይላንዱ ፊልም ስራ ላይ ተሳታፊ ስለነበር፣ የታይላንዱ ፊልም እዉቁን የአዉሮጻ የፊልም ስራ ሽልማት ማግኘት ጀርመናዉያኑን ማስደሰዙ አልቀረም። በካኑ የአለም አቀፍ የፊልም ፊስቲቫል የስድሳ ሶስት አመት ታሪክ የምርጥ ፊልም ስራ ወደ እስያ ሲሄድ ይህ የመጀመርያ እንደሆነም ተነግሮአል።
የካኑ የአለም አቀፍ የፊልም ፊስቲቫል ምርጥ የፊልም ተጫዋች ሲል ለፈረንሳይቷ የፊልም አክተር ስልማቱን ሲያበረክት ለስሆን ከወንዶች ምርጥ የፊልም ተጫዋች የስፔን ተወእ ማግኘታቸዉ ታዉቋል። ባለፈዉ እሁድ ምሽት በተጠናቀቀዉ በዘንድሮዉ የካን አለም አቀፍ የፊልም ፊስቲቫል የጀርመን ፊልም ምንም አይነት ሽልማትን ሳያገኝ አልቋል። በደቡባዊ የፈረንሳይ ጠረፍ ላይ የምትገኘዉ ካን ከተማ በያመቱ በሚደረገዉ የአለም አቀፍ የፊልም ፊስቲቫል ላይ ለምርጥ የፊልም፣ ለፊልም ስራ አዋቂዎች እና ተዋናዮች ሽልማትን በመስጠት እና እዉቅ ፊልሞችን በማየት ለሳምንት የሚዘልቅ ድግስን ያደርጋል። ፊስቲቫሉ ከፊልም ሽልማቱ ባሻገር የአለም ታዋቂ የሆኑ ተዋናዮች የዘመናዊ ልብስ ሰፊዎች፣ ልዮ የልብስ ቅድ ፣ባለሃብቶች ፣ ፖለቲከኞች የሚታዩበትም መድረክ ነዉ።

Apichatpong Weerasethakul für den besten Film mit der Goldenen Palme ausgezeichnet worden Cannes 63. Filmfestspiele Frankreich Gewinner
የ63 ኛዉ የካን አለም አቀፍ የፊልም ፊስቲቫል አሸናፊምስል AP

ሌላዉ በጀርመን የሶስት ቀናት የዘለቀ እና አንድ መቶ ሺህ እድምተኞች የጎበኙት የአፍራቃ ፊስቲቫል ተካሁዶአል። በባቫርያ ግዛት በቩርዝቡርግ ከተማ ባለፈዉ ሳምንት አርብ ጀምሮ እስከ ያዝነዉ ሳምንት ሰኞ ድረስ የዘለቀዉ የአፍሪቃ ፊስቲቫል የተለያዩ የአፍሪቃ አገሮች ባህላቸዉን፣ አልባሳትን ወግን እና የተለያዩ ባህላዊ ምግቦች የቀረቡበት መድረክም ነበር። ይህ ዘንድሮ ለ22ተኛ ግዜ በቩልዝቡርግ የተደረገዉ የአፍሪቃ ፊስቲቫል በተለይ የሚታወቀዉ እዉቅ አፍሪቃዊ አቀንቃኞችን በመድረኩ በመጋበዙ ነዉ። የበያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ ሰኞ በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ የጰራቅሊጦስ ወይም መንፈስ ቅዱስ ለሃዋርያት የተገለጠበት ቀን የተሰኘዉን የሃይማኖት በአል በማስመልክ በጀርመን የመንግስት መስሪያ ቤቶች ዝግ ሆነዉ በመዋላቸዉ የቩልዝቡርጉን የአፍሪቃ ፊስቲቫል በርካታ ህዝብ እንዲገኝ ሆንዋል ቀኑም ቢሆን ጸሃያማ እና ሞቃታማ ሆኖ ነበር የዋለዉ። በሌላ በኩል የዘንድሮዉን የአለም አቀፉን የእግር ዃስ ጨዋታ አስተናጋጅ ደቡብ አፍሪቃ በመሆንዋ የፊስቲቫሉ ዋነኛ ተጋባዥ እንግዳ ደቡብ አፍሪቃ እና የፊስቲቫሉ መድረክ የደመቀ አድርጎት እንደነበር ተነግሮአል። በአለም የሙዚቃ አፍቃሪዎች ዘንድ ታዋቂነትን ያተረፈዉ እና በጀርመናዉያን ዘንድ የአፍሪቃ አንባሳደር በመባል የሚታወቀዉ የሴኔጋሉ ድንቅ አቀንቃኝ ዩስንዱር የፊስቲቫሉን መድረክ በጥሩ ድምጹ መድረኩን ማንቀጥቀጡ ተነግሮለታል። ከትርኢቱ በዓላ በአፍሪቃ ተስፋፍቶ ስለሚገኘዉ ሙስናን በግልጽ መንቀፉ ተጽፎለታል። ነቀፊታ ብቻ አይደለም ሲኔጋለዊዉ ከያኒ ስለ አፍሪቃ፣ አፍሪቃ ድህነት ኤድስ ወይም ጦርነት ብቻ ሳይሆን በእድገት ላይ መሆንዋን በማስመስከር ላይ ናት ሲል መናገሩ በተለያዩ የባህል ድረ-ገጾች የቩርስቡርጉን የአፍሪቃ ፊስቲቫል በማስታከክ ተዘግቦበታል።
ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ጀርመን የአፍሪቃን ባህል ስታደንቅ የቆየችበት ሳምንት ሳይሆን አልቀረም በበርሊንም ቢሆን በርካታ ዳንሰኞች የተሳተፉበት የጎዳና ላይ ትርኢት በርካታ አፍሪቃዉያን መሳተፋቸዉ ተነግሮአል። ባለፈዉ ሰኞ እዚህ ጀርመን በጸራቅሊጦስ የክርስታና ሃይማኖት ተከታዮች በአል ምክንያት በማድረግ የእረፍት ቀን ሆኖ በመዋሉ በየአመቱ በበርሊን የሚደረገዉ ባህላዊ የጎዳና ላይ የጭፈራ በአል በደማቅ ሁኔታ ነዉ የተካሄደዉ። ከተለያዩ አገር የመጡ የበርሊን ነዋሪዎች እንዲሁም ጀርመናዉያን በየአመቱ የሚዘጋጁበት ይህ ህዝባዊ በአል ዘንድሮ በአርባ ዘጠኝ ቡድናት የተደራጁ የጎዳና ዳንሰኞች በቀለም የደመቀ አልባሳትን አድርገዉ በማዜም ከበሮ በመምታት እና የተለያዩ ዉዝዋዜዎችን ለእድምተኞች ማሳየታቸዉ ተገልጾአል። በርካታዉ ህዝብ ልብ የሳበዉ ታድያ የአፍሪቃዉ የዳንስ ትርኢት አልባሳት እና ከበሮ እንደነበርም ተገልጾአል።
«በበርሊኑ የጎዳ ዳንኪራ ለየት ያለ ነዉ። ሁኔታዉ ሁሉ ድንቅ የተባለዉን የብራዚሉን የጎዳና ዳንኪራ ማለት ካርናቫልን አይነት ነዉ። በርግጥ የከተማዉ ህዝብ በየአመቱ እንደ ብራዚሉ የጎዳና ዳንኪራ በጉጉት ባይጠብቀዉም እኛ የዳንሱ የጭፈራዉ ተሳታፊዎች እለቱን በጉጉት ነዉ የምንጠብቀዉ»
ትርኢቱን የተከታተሉት የበርሊኑ ከንቲባ ክላዉስ ቮቨራይትም ከተማቸዉ ከተለያዩ የአለም ክፍሎች የመጡ ህዝቦች የሚኖሩባት ልዮ ልዮ ባህሎችን ያቀፈች በመሆናቸዉ በኩራት ይገልጻሉ።
«ያሉትን የዳንስ ቡድኖች ማየት ይቻላል። ቡድኑ ዉስጥ ያሉት የዳንስ ተካፋዮች የመጡት ከተለያዩ የአለም አገሮች ነዉ። በጋራም ሲደንሱ ሲሰሩ ይታያል። ታድያ ሁኔታዉ ዳንሱ ጭፈራዉ መካሄዱ ብቻ ሳይሆን ህዝቦች በጋራ በመተሳሰብ እና በመግባታት አንድ ነገርን መፈጸማቸው ነዉ። በተጨማሪ በርሊን ከ 180 አገሮች የመጡ የተለያዩ ባህል ወግ ሃይማኖት ያላቸዉ ህዝቦች የሚኖሩባትም ነች»

Karneval der Kulturen 2010 in Berlin
በበርሊኑ የጎዳ ዳንኪራምስል DW/Wojcik

ወደ ሁለተኛዉ ርእሳችን ስንሻገር በኢትዮጽያችን በተለይ የናይሎ ሰሃራ ቋንቋ ዝርያ ይናገራሉ ከሚባሉት ብሄረሰቦች መካከል የኖር ብሄረብ የጸብ ማብረጃ የሰላም መጠበቅያ ባህላዊ ዘዴን በኢትዮጽያ የቋንቋ እና ባህል አካዳሚ ተጠሪ ዶክተር ባይለየኝ ጣሰዉ ጋር የተደረገ ዉይይት ነዉ ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ