1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የባህል መድረክ

ሐሙስ፣ ጥር 17 2004

የአዉሮጳዉ ህብረት አዲሱ የጎርጎረሳዉያኑ ዓመት በገባ የመጀመርያዉ ወር ከአዉሮጳ አገራት መካከል በሁለት አገራት ዉስጥ ያሉ ሁለት ከተሞችን የአመቱ የአዉሮጳ የባህል መዕከል ሲል ሰይሟል። ሌላዉ ርዕሳችን የፕረሽያዉ ንጉስ ዳግማዊ ፍሪድሪሽ ሶስመቶኛ አመት የልደር ቀን መታሰብያ መታሰብያ ነዉ።

https://p.dw.com/p/13qGd
Die 1743 errichtete Mariensäule in Maribor, aufgenommen am 26.03.2005. Maribor ist mit 108.000 Einwohnern die zweitgrößte Stadt in Slowenien. Die Siedlung wurde 1164 erstmals erwähnt.. Foto: Bernd Weißbrod dpa +++(c) dpa - Report+++
የዘንድሮ የአዉሮጳ ማዕከል ማሪቦር ከተማምስል picture-alliance/dpa

የአዉሮጳዉ ህብረት አዲሱ የጎርጎረሳዉያኑ ዓመት በገባ የመጀመርያዉ ወር ከአዉሮጳ አገራት መካከል በሁለት አገራት ዉስጥ ያሉ ሁለት ከተሞችን የአመቱ የአዉሮጳ የባህል መዕከል ሲል ሰይሟል። በቅርቡ አንድ ብሎ በጀመረዉ 2012 አ.ም የፖርቱጋልዋ ጉማራስ እና የስሎቬኒያዋን ማሪቦር ናቸዉ የአመቱ የባህል ማዕከል የተባሉ ከተሞች። ምስራቃዊ ስሎቬንያ ዉስጥ የምትገኘው ማሪቦር ከተማ የአልፕስን ሰንሰላታማ ተራራ ተንተርሳ የምትገኝ ኦስትርያን እና ክሮየሽያን የምታዋስን ጥንታዊት ከተማ ናት። በ15 እና በ16 ኛዉ ክፍለ ዘመን ዉስጥ የተገነቡ ታሪካዊ እና ጥንታዊ ቤቶች እንዲሁም የንጉሣዊ መቀመጫዎችን በብዛት በመያዟ የምትታወቀዉ የስሎቬንያዋ ማሪቦር ከተማ በአሁኑ ወቅት በበርካታ መኖርያ ቤቶች እና የሸቀጥ መደብሮች እንደተዋጠች ይነገራል። በዚህም ነዉ በከተማይቱ ጥንታዊ ባህላዊ እና ስነ-ጥበባዊ ቅርሶች እንዲታደሱ፤ ታሪካቸዉ እንዲወሳ ብሎም አገሪቱ በአዉሮጳዉያንም ሆነ በአለም ህዝቦች እንድትጎበኝ ለዘንድሮ የባህል ማዕከልነት የተመረጠችዉ።

የዕለቱ ሁለተኛ ርዕሳችን ደግሞ ትናንት በጀርመን ታስቦ ስለዋለዉ ስለ ፕራሽያዉ ንጉስ ዳግማዊ ፍሪድሪሽ ሶስመቶኛ አመት መታሰብያ ነዉ በእለቱ በአንደኝነት የያዝነው ርዕሳችን ነው። የዕለቱ ሁለተኛ ርዕሳችን ደግሞ የፕረሽያዉ ንጉስ ፍሪድሪሽ ዳግማዊ ሶስመቶኛ አመት የልደት ቀን መታሰቢያ በያዝነዉ ሳምንት ማክሰኞ ዕለት በርዕሰ ከተማ በርሊን በደማቅ መከበሩን ይሚያሳይው ዘገባ ነዌ። በአለም ዙርያ የፕረሽያ ንጉስ በመባል የሚታወቀዉ ፍሪድሪሽ ሁለተኛ ጀርመን በተለያዩ መሳፍንት ትገዛ በነበረበት ወቅት የትምህርት ተሀድሶን ያነቃቃ የዋሽንት ሙዚቃን አፍቃሪ የፕረሽያ ወይም ጀርመናዉያን እንደሚጠሩት ፕሮይሰን ንጉስ ነበር። በጎርጎረሳዉያኑ አቆጣጠር ከ 1712 አም እስከ 1786 አ.ም ድረስ የኖረዉ ዳግማዊ ፍሪድሪሽ ጀርመናዉያን አልተ ፍሪትዝ ሲሉ በቅጽል ስሙም ይጠሩታል። የፕረሽያ ንጉስ የፍሪድሪክ ዳግማዊ ሶስት መቶኛ ዓመት መታሰቢያ በርሊን በሚገኘዉ እዉቅ የሙዚቃ አዳራሽ ሲታሰብ የጀርመኑ ርዕሰ ብሄር ክርስትያን ቩልፍ ከፖለቲካዉ፣ እና ከተለያዩ የማህበረሰቡ ክፍሎች ተጋባዥ የሆኑ አንድ ሽ ሁለት መቶ እንግዶች በተገኙበት ህብረተሰቡ ታሪክን በተለያየ ገጽታዉ እንዲመለከት ጥሪ አድርገዋል። ፕሪዝደንት ቩልፍ በመታሰቢያዉ በአል ላይ ባሰሙት ንግግር የፕሪሽያዉን ንጉስ ሥራዎች በአንድ ገጽታዉ ብቻ ማየት የለብንም ብለዋል

«ስልጣኑን ለማስጠበቅ ሲል ትልቅ ጦርነት ያካሄደ ነዉ፣ በሌላ በኩል የተላበሰዉ ትዕግስት እና ሁሉን እኩል የሚያይበት አቋሙ በአንድ ላይ ሁኔታዉን የአንድ ሳንቲብ ገጽታ ያደርገዋል። በዚህም በአንድ በኩል በጣም ጠንካራና ሃይለኛ ሲሆን በሌላ መልኩ ደግሞ ለስላሳ ጥሩ ዋሽንት ሙዚቃኛ ነበር»

Flash-Galerie Friedrich der Große
በበርሊን የሚገኘዉ የፕረሽያዉ ንጉስ ዳግማዊ ፍሪድሪሽ ሃዉልትምስል Fotolia/ArTo

ዳግማዊ ፍሪድሪሽ በስልጣን ዘመኑ የእስልምና እና የክርስትና እንዲሁም የፈረንሳይ የፕሮቲስታንቶችን እምነት በማክበር የተቀበለ ነበር። ዳግማዊ ፍሪድሪሽ ይህን የተለያየ እምነት የነበራቸዉን ህዝቦች አገሩ እንዲኖሩ ተቀብሎአል። ይህን ያደረገበት ዋናዉ ምክንያትም አስተዳደሩ ግዛቱን ለማስፋት ባካሄደዉ ከባድ ጦርነት ከፍተኛ የህዝብ እልቂት ስለተከሰተ እና የፕራሽያ አስተዳደርን የሚጠቅም ሁኔታን በማየቱ እንደነበርም ይነገራል። በዚህም የፕራሽያዉ ንጉስ የዳግማዊ ፍሪድሪክ ታሪክ እንደ አንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ እንዲኖረዉ ያደርገዋል ተብሏል። ሙሉዉን ቅንብር ያዳምጡ!

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ