የቢላል ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት አለመቅረባቸዉ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 8 2005ማስታወቂያ
የራዲዮዉ ከፍተኛ አዘጋጅ ዳርሰማ ሶሪ እና የዜና አዘጋጅ የሆነዉ ኻሊድ መሐመድ ክስ ሳይመሠረትባቸዉ እስር ላይ እንደሚገኙ ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተዉ ዓለም ዓቀፉ ድርጅት CPJ አስታዉቋል። የታሰሩትን ጋዜጠኞች አግኝቶ ማነጋገር እንዳልተቻለ የገለጹልን የህግ ባለሙያና ጠበቃ አቶ ዳዊት ነጋሽ ይቀርቡበታል በተባለዉ ፍርድ ቤት ዛሬ ለረዥም ሰዓታት መጠበቃቸዉን አመልክተዋል። ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ የሕግ ባለሙያዉን በስልክ አነጋግሬያቸዋለሁ፤
ሸዋዬ ለገሠ
ሂሩት መለሰ