1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቡድን 8 ጉባኤ ፍፃሜ ና አቶ መለስ

ሰኞ፣ ግንቦት 13 2004

የቡድን 8 አባል ሃገራት በአፍሪቃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የልማት ትብብር ለማድረግ ቃል ገቡ ። በኢንዱስትሪ የበለፀጉት 8 የዓለም ሃብታም ሃገራት በካምፕ ዴቪድ ሜሪላንድ ክፍለ ግዛት ባካሄዱት ጉባኤ እንዳሳወቁት የልማት እርዳታው ግብ አፍሪቃን

https://p.dw.com/p/14zP4
ምስል dapd

ከእርዳታ ጠባቂነት አላቆ በምግብ ራስዋን እንድትችል ማድረግ ነው ። አፍሪቃን ከእርዳታ ጠባቂነት አላቆ በምግብ ራስዋን እንድትችል ማድረግ ነው ። በተለይ በዚህ ጉዳይ ላይ ባተኮረው ሲምፖዚየም ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለሰ ዜናዊ አብዛኛው ህዝብ የሚተዳደርበትን ግብርናን ማሳደግ ዋና ትኩረታቸው መሆኑን ተናግረዋል ። አቶ መለስ በሲምፖዝየሙ ላይ የሰጡት ማበራሪያ በአንድ ጋዜጠኛ ተቃውሞ ተቋርጦ ነበር ። ኢትዮጵያውያን በካምፕ ዴቪድ የተቃወሞና የድጋፍ ትዕይንትም አካሂደዋል ። ዝርዝሩን አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዲሲ ልኮልናል ።

አበበ ፈለቀ

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ