የቡድን 7 ጉባዔ በቶርሚና ኢጣልያ
ዓርብ፣ ግንቦት 18 2009ማስታወቂያ
ብሪታንያ ማንችስተር ላይ የሽብር ጥቃት መድረሱን ተከትሎ ጉባዔዉ ሽብርተኝነትን መዋጋት» የሚለዉን ርዕሱ እንደሚያደርግ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ጉባዔዉ አጨቃጫቂ የተባሉትን የንግድ ልዉዉጥና የአየር ንብረት ለውጥ ርዕሶችንም ያነሳል። በቡድን ሰባት ጉባዔ ላይ ለመጀመርያ ጊዜ የሚሳተፉት አዲሱ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሃገራቸዉ አምና ፓሪስ ላይ ከፈረመችዉ የሙቀት አማቂ ስጋቶች ቅነሳ ስምምነት እንደምትወጣ እና በብሔራዊ ፍላጎት ላይ ያተኮረ የንግድ ፖለቲካ ላይ እንደምታተኮር ተናግረዋል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ ግን የዩኤስ አሜሪካ መንግሥት እስካሁን ምንም ዓይነት ዉሳኔ አላስተላለፈም። በኢጣልያ የሮም ወኪላችን ተኽለዝጊ ገብረየሱስ ዛሬ ቶርሚና ላይ ስለተጀመረዉ የቡድን ሰባት ጉባዔ ዘገባ ልኮልናል።
ተኽለዝጊ ገብረየሱስ
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ